Jump to content

ደን

ከውክፔዲያ
(ከደን ሰምቲ የተዛወረ)
ይህ መጣጥፍ ስለ ፈርዖኑ ደን ነው። ለብዙ ዛፎች መሬት ጫካን ይዩ።
ፈርዖን ደን ከደቂቃ ሴት ዓላማ በታች የሆነውን ጠላት በዱላ ሲመታ።

ደን የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት (1ኛው ሥርወ መንግሥት) ፈርዖን ነበረ። ስሙ «ደን» ለመጀመርያው ጊዜ የስዕል ቃል ሳይሆን እንደ ፊደላት ለተናባቢ በሚጠቅሙ ምልክቶች (ደ፣ ነ)

D46n

ተጻፈ። ሌላ ስም ሰምቲ ነበረው፣ ይህ ግን በስዕል ቃል ተጻፈ። በልጅነቱ ንጉሥ ሆኖ እናቱ መርኒት እንደራሴ ሆና ገዛች።

በስመቲ ዘመን የአባይ ሸለቆ ሕዝብ ቁጥር እጅግ ስለ በዛ ብዙ ሕንጻዎች ተሠሩ። በመቃብሩ አንድ ማኅተም የሥርወ መግሥቱ ፈርዖኖች ይዘርዝራል፦ ናርመር፣ አሃ (1 ቴቲ)፣ ጀርጀት፣ ደን እና መርኒት። ከያንዳንዱ ንጉሥ ስም በፊት «ቀንታመንቲው ሔሩ» የሚለው አርዕስት ይታያል። እነኚህ የአረመኔ ጣኦታት ስሞች ነበሩ። 136 ሎሌዎች ደግሞ ከሰምቲ ጋራ ተቀበሩ።