የሀረም ጽሕፈቶች
Appearance
የሀረም ጽሕፈቶች በጥንታዊ ግብፅ መንግሥት ሀረሞች (ፒራሚዶች) ውስጥ፣ በውስጣዊ ግድግዳዎች ላይ የተቀረጹ የሃይሮግሊፍ መዝሙሮች ናቸው። እነዚህ አረመኔ መዝሙሮች ከ2845 ዓክልበ. ግ. ጀመሮ ተጽፈው[1]፣ እስከሚታስብ ድረስ ከዓለሙ መጀመርያው ሃይማኖታዊ ሰነዶች እነዚህ ናቸው።[2] ጽሑፉ ሲተረጐም፣ የ«ሔሩ» ተከታዮች ወገን (ወይም ደቂቃ ሔሩ) በ«ሴት» ተከታዮች ወገን ላይ የፈጸመውን ጨካኝ የጭራቅነት ሥነ ስርዓት የሚመሠክር ነው። በጥንታዊ ግብፅ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ይኸው ሴትና ቄንቲያመንቱ (ዖሴሮስ) ወንድሞች ሲሆኑ፣ ሔሩ የቄንቲያመንቱ ልጅ ነበረ። የጥንቱ መንግሥት ፈርዖኖችም ከሔሩና ከሴት ውኅደት እንደ ተወለዱ ያምኑ ነበር።
- Wolfgang Kosack: Die altägyptischen Pyramidentexte. In neuer deutscher Uebersetzung; vollständig bearbeitet und herausgegeben von Wolfgang Kosack Christoph Brunner, Berlin 2012, ISBN 978-3-9524018-1-1.
- ^ The Ancient Egyptian Pyramid Texts
- ^ Richard H. Wilkinson, The Complete Gods and Goddesses of Ancient Egypt, Thames and Hudson, New York, 2003, p 6