Jump to content

አንጎል

ከውክፔዲያ
የ16:36, 2 ጁላይ 2021 ዕትም (ከ196.188.241.7 (ውይይት) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ቺምፓንዚ አእምሮ

አንጎልማዕከላዊ ስርዓተ ነርቭ ክፍል ሲሆን የሚገኘውም በራስ ቅል አጥንት ውስጥ ነው። በራስ ቅል መሸፈኑ በምንም ዓይነት የመታየት የመነካት የመሸተት አልያም የመቀመስ እድል እንዳይኖረው አድርጎታል። ይህ መዋቅር የሚገኘው በዋናነት የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ላይ ሲሆን በአብዛሀኛዎቹ የጀርባ አጥንት የሌላቸው እንስሳት ላይም ይገኛል። በአንዳንድ እንደ ኮከብ ዓሳ ያሉ የዓሳ ዝርያዎች ላይ ይህ አካል የሌለ ሲሆን እንደ ስፖንጅ (Sponges) ዓይነት እንስሳቶች ደግሞ ጭራሹንም የስርዓተ ነርቭ መዋቅር የላቸውም።

ከሳይንስ አንጻር አእምሮና አንጎል ይገናኛሉ ተብለው ሲታመን ለዚህ እንደ ዋና ማስረጃ ሆኖ የሚቀርበው በተጨባጩ የአንጎል ክፍሎች ላይ የሚደርስ ጉዳት በአእምሮ (አስተሳሰብ) ላይ የሚያመጣው ለውጥ ነው። ሌላው ተጠቃሽ መረጃ አንድ አንድ መድሃኒቶች በአእምሮ ላይ የሚያመጡት ለውጦች ናቸው።