እርዳታ:የማዘጋጀት እርዳታ

ከውክፔዲያ
(ከእርዳታ:Editing የተዛወረ)

በፊደል አጻጻፍ ዘዴ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጽሁፍ ገጹ ላይ በቀጥታ በፊደል አመታቱ ኢትዮፒክ ሴራ ተብራርቷል።

አዲስ ገጽ መፍጠር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • በውክፔድያ ላይ አዲስ ገጽ ወይም ፅሑፍ ለመፍጠር፣ በግራ ያለው «ፍለጋ ሳጥን» ይጠቅማል። የአርዕስትዎ መጣጥፍ ገና ያልኖረ እንደ ሆነ፣ «ፍለጋ»ም እንደ ተጫነ፣ «የፍለጋ ውጤቶች» በሚለው ገጽ ሥር «_______ የሚባል መጣጥፍ ይፈጠር?» አለ። አርዕስትዎም እንደ «ቀይ መያያዣ» ሲታይ ሊጫኑት ይችላሉ። ቀይ መያያዣውን በመከታተል «ይኸው ገጽ ገና አይኖርም...» በሚለው ገጽ ላይ በቀጥታ ለመጻፍ ሊጀምሩ ይቻሎታል።
  • አለዚያ፣ በሌላ ጽሑፍ የፈለጉትን ገጽ አርእስት በፊደል አውጥተው ስሙን በ[[ ]] ውስጥ አድርገው፣ ከቀረበው በኋላ የመረጡት አርእስት ቀድሞ ባይኖር፣ ቀይ መያያዣ ይፈጠራል።

የቆየውን ገጽ እትም መለወጥ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቀጥታ በሳጥኑ ውስጥ ያቀነባብሩት ወይም ያጣብቁበት («paste» ያድርጉበት)። እየሠራኸው ምን እንደ ጻፉ የረሱ እንደ ሆነ፤ ከታች የሚገኘው «ማነጻጸሪያ» ያለውን ምልክት ይጠቅሞታል።

ገጹ ከነለውጦችዎ ምን እንደሚመስል ለማወቅ፣ «ቅድመ እይታ» ያለውን ይጫኑ። ይህ ለሙከራ ብቻ እንጂ ለውጦቹን ወደ ዊኪፔድያ የሚያቀርብ አይደለም።

«ማጠቃለያ:» በሚለው ሕዋእ አጠገብ ለሌሎች አዘጋጆች የሚታይ ማንኛውንም አስተያየት መጻፍ ይችላሉ። ኣብዛኛው ጊዜ፤ ይህ ስለ ለውጦችዎ መግለጫ ይሆናል እንጂ አስፈላጊ አይደለም። ማጠቃለያው የሚታይበት በገጹ እትም ታሪክ ይሆናል።

ወደ አባልነት ከገቡና ለውጥዎ በጣም ቁም ነገር የማይሆን ትንንሽ ፊደል ወይም አንዳንድ ነጥብ በማስተካከል ብቻ ከሆነ፣ «ይህ ለውጥ ጥቃቅን ነው» በሚለው አጠገብ ምልክት ማድረግ ይችላሉ። ይህ አስፈላጊ አይደለም፣ ነገር ግን ጥቃቅኖቹን ለመሠውር ለሚያስብ አዘጋጅ ስለሚረዳ እንደ ጨዋነት ይቆጠራል።

ደግሞ ለአባላት «የምከታተላቸው ገጾች» የሚባል ልዩ ገጽ አለ። እዚያ ላይ፣ አባሉ የመረጣቸውን ገጾች ሁሉ ሲለወጡ በዝርዝር ሊከታተላቸው ይችላል። አባል ሆነው የሚያዘጋጁት ገጽ በዚያው ዝርዝር እንዲጨመር ሲፈልጉ፤ «ይህንን ገጽ ለመከታተል» ከሚለው አጠገብ ምልክት እንዳለ ያረጋግጡ። ወይም ይህ ባይሆን ገጹ ወደዚያው እንዳይጨመር ቢሻልዎ፣ ምልክቱን ያጥፉት።

በማንኛውም ጊዜ ማዘጋጀቱን ሊሠርዙት ይችላሉ። ለዚሁ ምክንያት «ይቅር! (ለመሰረዝ)» የሚለው መያያዣ አለ።

ተጨማሪ የጽሁፎችን አጻጻፍ ዘዴ ለማየት እዚህ ይሂዱ

ተጨማሪ የጽሁፎችን፡ አጻጻፍ፡ ዘዴዎች በእንግሊዝኛ፡ ለመማር፡ እዚህ፡ ይሂዱ።