Jump to content

መሺካ

ከውክፔዲያ

መሺካ በዛሬው ሜክሲኮ የኖረ የአዝቴክ መንግሥት ኗሪ ገዢዎች ብሔር ነበሩ።

መሺካ ናዋ ብሔሮች ሲሆኑ ሁለት ከተሞቻቸውን ቴኖሕቲትላንትላተሎልኮተክስኮኮ ሐይቅ ደሴቶች ላይ በ1200 ዓም ያህል መሠረቱ። «የአዝቴኮች ሦስትዮሽ ጓደኝነት» ከተዋዋሉ በኋላ የቴኖሕቲትላን መሺካ ኗሪዎች በሌሎቹ ፪ ከተሞች በተክስኮኮና በትላኮፓን ላይ ልዑላን ሆኑ።

የዛሬ ሜክሲኮ አገር ስያሜ የደረሰ ከ«መሺካ» ነው። የእስፓንያ ሃያላት አገሩን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ከያዙ በኋላ ስሙን «አዲስ እስፓንያ» አሉት።

የመሺካ ቋንቋ ናዋትል ሲሆን እስካሁን ድረስ 1.5 ሚሊዮን ተናጋሪዎች አሉት።

ሕዊፂሎፖቅትሊ የመሺካዎች አምላክ
  • Andrews, J. Richard (2003). Introduction to Classical Nahuatl (rev. ed.). Norman: University of Oklahoma Press. ISBN 0-8061-3452-6.