ሙቀት
Appearance
ሙቀት በተፈጥሮ ህግ ጥናት ከአንድ ቁስ ወደ ሌላ ቁስ ያለምንም ስራ አቅም ሲተላለፍ ማለት ነው። ባጭሩ ለማስረዳት፣ አንድ ሰው ትልቅ ድንጋይ ወደላይ ቢያነሳ በዲንጋዩ ላይ ስራ ሰርቷአል ምክንያቱም የሰውየው ጉልበትና ድንጋዩ የተጓዘበት አቅጣጫ አንድ አይነት ስለሆነ። እንግዲህ ድንጋዩ ከፍተኛ ቦታ ላይ ሰለሆነ ያለው ቢለቀቅ ስራ ሊሰራ ይችላል፤ ይህም አቅም ከሰውየው ወደ ድንጋዩ ስራ ተላልፏል ማለት ነው። ለአቅሙ መተላለፍ ስራ ስለተሰራ ትልልፉ ሙቀት አይባልም። ባንጻሩ ድንጋዩን ፀሐይ ላይ ብንተወው እየጋለ ይሄዳል። ይህ ግለት ውሃ እላዩ ላይ ጠብ ቢልበት በማትነን በውሃ ላይ ስራ መስራት ይችላል። ይህ የሚያሳየው አቅም ከፀሐይ ወደ ድንጋዩ መተላለፉን ነው። ነገር ግን ፀሐዩዋ ድንጋዩን ስላላንቀሳቀሰችው ስራ አልሰራችበትም። ስራ ሳይሰራ የሚደረገው የአቅም ልውውጥ ሙቀት ይባላል።