ሰኔ ፳፫
Appearance
(ከሰኔ 23 የተዛወረ)
ሰኔ ፳፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፺፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፸፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፸፪ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፶፭ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ገላውዴዎስ በዘመኑ የካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን <<ኦሪታዊ’ ናት>> እያሉ ስም የማጥፋት ዘመቻቸውን በመከላከል፣ ዳሞት ላይ የተጻፈ የሃይማኖቱን እውነትነት የሚገልጽ ውሳኔ ፈረመ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የፋሺስታዊ ኢጣልያ ሠራዊት ኢትዮጵያን በግፍ ወሮ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ እና ንጉሠ ነገሥቷ ከተሰደዱ በኋላ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዠኔቭ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ማኅበር ላይ ተገኝተው የኢጣልያን ግፈኝነትና የኢትዮጵያን አቤቱታ አሰሙ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኮንጎ ሪፑብሊክ (ኮንጎ ሊዮፖልድቪል/የቤልጂግ ኮንጎ) ከቤልጂግ ቅኝ ግዛትነት ነፃነቷን አወጀች። ዮሴፍ ካዛቩቡ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።
- http://ethiopianorthodox.org/amharic/miscellenous/betekirstiansetefeten/abbawtinsae/claudiusdeclaration.pdf
- (እንግሊዝኛ) Dugan, James and Lafore, Laurence; "Days of Emperor & Clown"; Doubleday (1973), p 292