Jump to content

ሲን-ኢዲናም

ከውክፔዲያ
ከ1754 ዓክልበ. የሆነ መሠረት ድንጋይ ማዕረጉን «ንጉሥ ሲን-ኢዲናም፣ ሁሉንም ነገር ለኒፑር ያጌጠው እረኛ፣ የኡር መጋቢ፣ የላርሳ ንጉሥ፣ የሱመርና የአካድ ንጉሥ» ይሰጣል።

ሲን-ኢዲናም ከ1760 እስከ 1753 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የላርሳ 5ኛ ንጉሥ ነበረ። የኑር-አዳድ ልጅና ተከታይ ነበር።

ሲን-ኢዲናም በመጀመርያው ዓመት ምናልባት ከአባቱ ኑር-አዳድ ጋራ የጋርዮሽ ንጉሥ እንደ ነበር ይመስላል።

ለዘመኑ ፯ ዓመታት ሁላቸው የዓመት ስሞች ታውቀዋል። እነርሱም፦

1760 ዓክልበ. ግ. - «ሲን-ኢዲናም ንጉሥ የሆነበት ዓመት»
1759 ዓክልበ. ግ. - «ጤግሮስ ወንዝ የተቆፈረበት ዓመት»
1758 ዓክልበ. ግ. - «ቤተ መቅደስ የተመሠረተበት ዓመት»
1757 ዓክልበ. ግ. - «የባቢሎን ሥራዊት በመሣሪያዎች የተመታበት ዓመት»
1756 ዓክልበ. ግ. - «(ሲን-ኢዲናም) ኢብራትና ማልጊዩምና ሌሎች ከተሞች የያዘበት ዓመት» / «ማልጊዩም በመሣርያዎች የተመታበት ዓመት»
1755 ዓክልበ. ግ. - «የኤሽኑና ምድር የጠፋበት ዓመት»
1754 ዓክልበ. ግ. - «የማሽካን-ሻፒር ታላቅ ከተማ ግድግዳ የተሠራበት ዓመት»
1753 ዓክልበ. ግ. - «ሲን-ኤሪባም ንጉሥ የሆነበት አመት»

በሲን-ኢዲናም መጨረሻ ዓመት ኒፑር (የሱመርና የአካድ ዋና ከተማ) ከኢሲን ወደ ላርሳ ግዛት እንደ ተመለሰ ይታወቃል። የሲን-ኢዲናም ተከታይ ሲን-ኤሪባም ነበረ። የሲን-ኤሪባም አባት ስም አይታወቅም።

ሲን-ኢዲናም እንደ ጽድቅ ንጉሥ ተቆጠረ፤ ከመሞቱም በኋላ እስከ ሪም-ሲን ዘመን (1734-1675 ዓክልበ.) እንደ አምላክ ተቆጠረ።

ቀዳሚው
ኑር-አዳድ
ላርሳ ንጉሥ
1760-1753 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሲን-ኤሪባም

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]