Jump to content

ስቲግማ

ከውክፔዲያ
የግሪክኛ የተያያዘው ፊደል «ስቲግማ»

ስቲግማ (στίγμα) በመጀመርያ በግሪክኛ ቋንቋ «ምልክት»፣ «ነጥብ» ማለት ነበር።

የ መሣርያ ከተፈጠረ ጀምሮ፣ በግሪክኛ ሁለት የተያያዙ ፊደላት ለመጻፍ አንዳንድ ligature («ሊጋቹር» ወይም የተያያዘ ፊደል) ይጠቀም ነበር። ከነዚህ አንዱ ሊጋቹር የፊደሎች «» () እና «» () አንድላይ ሲታዩ በ«στ» ፋንታ የተያያዘው ፊደል «ϛ» («ስቲግማ») ተባለ። ስሙ የተነሣ በከፊል የቃሉ ፍች «ምልክት» ስለ ሆነ፣ በከፊልም የ«ስ» እና «ት» ድምጾች ለማመልከት «ሲግማ» የሚለውንም ስም ለመምሰል ነበር።

በዚህ ደረጃ፣ የ«ስቲግማ» ቅርጽ እና የ«» ቅርጽ ተመሳሳይ ነበሩ። የ«ዲጋማ» ታሪክ ግን ከ፮ናው ሴማዊው ፊደል ዋው ነበር። በጥንት ይህ ተናባቢ ግሪክኛን ለመጻፍ የማያስፈልግ ሆነ፤ ስለዚህ ስድስተኛው ፊደል ቁጥሩን «ስድስት» ለመጻፍ ብቻ በቃ። በኋላ ትርፉ ፊደል «ዋው» ϝ ሲጻፍ፣ «ጋማ» (Γ) በመምሰሉ ስያሜው «ዲጋማ» («የሁለት ድርብ ጋማ») ሆነ። ስለዚህ ሁለቱ ምልክቶች «ስቲግማ» እና «ዲጋማ» እንደ ϛ በተጻፉበት ጊዜ፣ የቁጥሩ ስድስት ምልክት ደግሞ በግሪክኛ «ስቲግማ» ይባል ጀመር።

በጊዜ ላይ፣ የ«ስቲግማ» ጥቅም በተለይ ቁጥሩን «ስድስት» (ግሪክኛ፦ /ሄክስ/) ለመጻፍ ብቻ ሆነ፣ እንጂ ለፊደላት «στ» ለማመልከት በብዛት አልታየም ነበር። ዛሬም ምልክቱ እራሱ (ϛ) አልፎ አልፎ ብቻ ስለሚታይ፣ ቁጥሩ ስድስት በዚህ ታሪክ ከ«ስቲግማ» ጋር ግንኙነት ስላገኘው፣ ቁጥሩን ስድስት ለመጻፍ በዘመናዊ ግሪክኛ በሁለቱ ፊደላት እንደ «στʹ» ይጻፋል።

ከ«ስቲግማ» መጀመርያ ግሪክኛው ትርጉም («ምልክት») የተነሣ ደግሞ፣ በዘመናዊ ልሳናት «መጥፎ ይሉኝታ»፣ «መገለል»፣ «ስድብ» ወይም «እርም» የመሰሉትን ትርጉሞች አሉት። ይህ በጥንት የመተኮስ ምልክት እንደ ቅጣት ስለ ጠቀመ ነበር።