በር:ፍልስፍና/የተመረጠ ጽሑፍ/34
Appearance
< በር:ፍልስፍና
ሬኔ ደካርት (René Descartes) (መጋቢት 31፣ 1596 – ሐምሌ 1650;) ፈረንሳዊ ሳይንቲስት፣ ሂሳብ ተመራማሪ እና ፈላስፋ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የምዕራቡን አለም አዲሱን ፍልስፍና መስራች (የአውሮጳ ፍልስፍና አባት) በመባል ይታወቃል። የዚህ አባባል ምክንያቱ በኋላው የተነሱት ፈላስፎች እርሱ ባነሳቸው ነጥቦች ላይ ወይ ተቃውመው ወይም አስፋፍተው በመጻፍቸው እና እሱ ካነስቸው ጽንሰ ሃስቦች የተለየ አዲስ ነገር ስላልገኙ ነው። ከፍልስፍና ጽሁፎቹ ውስጥ አትኩረተ ህሊና በፍልስፍና መሰረት ላይ (Meditations on First Philosophy) የተባለው ጽሁፉ እስካሁን ዘመን ድረስ በዩንቨርስቲወች ውስጥ እንደ ዋና የትህርት ክፍል ይሰጣል። ደካርት የምክኑያዊነት(rationalism) ፍልስፍና ተከታይ ነበር። ምክኑያዊነት፣ አስተያየቶችና እምነቶች ከሁሉ በፊት በምክንያትና በ ዕውቀት ላይ መመሥረት አለባቸው የሚል ነው። ሃይማኖት እና ሥሜታዊነት የምክንያት ውጤቶች እንዲሆኑ የሚጥር አስተሳሰብ ነው።