Jump to content

ቤቱስ

ከውክፔዲያ

ቤቱስእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ከታጉስ ኦርማ ቀጥሎ የኢቤሪያ 6ኛው ንጉሥ ነበረ (ምናልባት 2081-2055 ዓክልበ. ግድም)። ቤቱስ የታጉስ ልጅ ይባላል። በእስፓንያ የሚፈስሰው ቤቲስ ወንዝ (አሁን ጓዳልኪቪር ወንዝ) ስለእርሱ እንደ ተሰየመ የሚሉ መጻሕፍት አሉ። በሌላ በኩል የቤቱስ ሁለተኛ ስም «ቱርዲታኑስ» ሲሆን ቤቲካቱርደታኒያ የተባሉት ክፍላገራት ከእርሱ ተሰይመው ነበር። በአባቱ ዘመን አገሩ «ታጋ» እንደ ተባለ አሁን የመንግሥት ስም «ቱርደታኒያ» ሆነ። ቤቱስ ሕግ፣ ጽሕፈትና ትምህርት ወደ አገሩ እንዳስገባ ይባላል።

ባንዳንድ ምንጭ በዘመኑ ጌርዮን (ደያቡስ) ከስሜን አፍሪቃ መጥቶ በአሁኑ ገዲር ዳርቻ አጠገብ ባለ ደሴት ላይ ሠፈረ፣ በኋላም ዙፋኑን ከቤቱስ ያዘው። (ይኸው ደሴት ኤሪጠያ ወይም «ዩኖኒያ»፣ «ኤርኒያ» «ኤርትራ» ተብሎ በሮሜ ንጉሥ ቫሌንስ ዘመን 356-370 ዓ.ም. በምድር መንቀጥቀጥ በውቅያኖስ እንደ ሰመጠ ይባላል።) [1] ሌሎች እንደሚሉ ትልቅ የሊብያና የግብጽ ሠራዊት በቤቱስ ዘመን አገሩን ወርሮ ደቡብ-መዕራብ ክፍሎቹን ይዞ ነበር።


ቀዳሚው
ታጉስ ኦርማ
የቱርደታኒያ ንጉሥ ተከታይ
ጌርዮን
  1. ^ A Civil, Commercial, Political, and Literary History of Spain and Portugal