Jump to content

ብይ

ከውክፔዲያ

ብይ የኢትዮጵያ ህጻናት ትንሽ ድቡልቡል ነገርን (ከእስክፒቶ ቀፎ በማቅለጥና በጅ በማበልበል የሚሰራ ወይም ደግሞ ለዚሁ ተብሎ ከሚሰራ "ብይ" ወይም ከኩቺኔታ ኳሶች የሚሰራ) የተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ በመክተትና ከዚያም የተቃራኒን ብዮች በማጥቃትና በ"መብላት" የሚጫወቱት ነው። ጎበዝ የብይ ተጫዋች ጉድጓድ መግባትና ከዚያም የባላጋራውን ብይ አነጣጥሮ በመምታት መብላት ሳይሆን አንድ አንድ ጊዜም የተቃራኒውን ብይ መስበር ወይም መፈርካከስን ያጠቃልላል። ይህ ጨዋታ ለህጻናት ብዙ ትምህርት ይሰጣል።

በክፍለ ሀገር ያሉ ህፃናት ብይ ከጭቃ በመስራት ይጫወቱ ነበር።

መደብ ጨዋታ