ታራጎና
Appearance
ታራጎና Tarragona | |
የታራጎና ዕይታ | |
ክፍላገር | ካታሎኒያ |
ከፍታ | 68 ሜ. |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 140184 |
ታራጎና (እስፓንኛ፦ Tarragona) የእስፓንያ ከተማ ነው።
ከሮማውያን አስቀድሞ ኢቤራውያን ከጥንት ይሠፍሩበት ነበር። በአንድ አፈ ታሪክ ዘንድ ቶቤል በ2415 ዓክልበ. ስለ በኲሩ «ታራሆ» ስም መሠረተው። ሌላ ተረት ደግሞ እንደሚለው የግብጽ፣ ኩሽና ኢትዮጵያ ፈርዖን ታርሐቃ (700 ዓክልበ. ግድም) በዚህ ዘምቶ ያቆመው ነው። ለነዚህ ታሪኮች ግን ታማኝ መዝገብ የለም። ዊሊያም ስሚስ እንደ ገመተ ከተማው በፊንቄ ሰዎች ተሠርቶ በቋንቋቸው ጣርቆን አሉት። የሮማውያን አለቃ ስኪፒዮ አፍሪካኑስ በ225 ዓክልበ. ዙሪያውን ይዞ በሥፍራው ታራኮ የተባለ ከተማ አሠራ።