Jump to content

ቴክሳስ

ከውክፔዲያ

ቴክሳስአሜሪካ ከሚገኙ 50 ግዛቶች አንዱ ሲሆነ በስፋቱም ሆነ በህዝብ ብዛቱ በሃገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ግዛቶች ሁሉ ሁለተኛ ነው። ይህም ማለት ከካሊፎርኒያ ከጥላ ማለት ነው። የቴክሳስ ስም የመጣው ቴካስ ከሚለው የካኡው ነገድ ሲሆን ትርጉሙም ጓደኛ ወይም ባለ ቃልኪዳን ማለት ነው። ቴክሳስ ተገንጣይዋ ኮከብ ማለትም ነው፤ ይህ ብቻ አይደለም ቴክሳስ የራሷ የሆነ ባንዲራ እና ወሰንም ነበራት። ቴክሳስ በስፋቷ ትልቅ በመሆኗ በእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ግዙፍ የሚል ትርጓሜ አለው። ቴክሳስ በኢንዲያውያን ነገዶች ስትገዛ የኖረች ስትሆን ስፔን የመጀመሪያዋ ሀገር ነበረች ቴክሳስን ለማጠንከር የፈለገችው ስለዚህም በ 1820 አውሮፓውያንን በማስገባት የበለጠ ኗሪ እና ጠንካራ ህዝብ እንድትሆን አድርጋት ገዝታት ነበር ነገር ግን በ 1821 ቴክሳስ ከስፔን ግዛት ነጻ መሆኗን ሜክሲኮ አውጃ በራሷ በሜክሲኮ አገዛዝ ስር አደረገቻት። በ 1836 በማርች ወር ከሜክሲኮ ግዛት ነጻነቷን አወጀች። በ 1845 በአሜሪካ ፌዴራላዊ የተባበሩት ሀገራት መንግስት 28 ሀገር በመሆንና 4ኛዋ ከጥምር በፊት የራሷ የሆነ ስልጣን ያላት ሀገር መሆን ችላለች። በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ ቴክሳስ ውስጥ ነዳጅ ተገኘ ይህም የቴክሳስ ኗሪወች ቁጥር እንዲቸምርና ኒው ዮርክን በመብለጥ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ ሀገር እንድትሆን ያደረጋት።