ኅዳር ፲፭
Appearance
ኅዳር ፲፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፭ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፩ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺ ቀናት ይቀራሉ።
፲፱፻፶፮ ዓ.ም. ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል ተብሎ የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ ዳላስ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችና ቴሌቪዝን ድርጊቱን ለዓለም እየሰራጩ ሳሉ፤ ጃክ ሩቢ የሚባለው ሰው ኦዝዋልድን በሽጉጥ ገደለው።
፲፱፻፶፰ ዓ.ም. አምባገነኑ ጆሴፍ ዴዚሬ ሞቡቱ በኮንጎ የመሪነትን ሥልጣን በጉልበት ጨበጠ። በ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የአገሪቱን ስም ቀይሮ ዛይር ተባለች። እሱም በአምባገነነንነት ሠላሣ ሁለት ዓመታት ከገዛ በኋላ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. በኃይል ከሥልጣን ተወገደ።
፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ዶናልድ ዮሃንሰን እና ቶም ግሬይ አፋር ክልል ውስጥ ከ ሦሥት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖረችውን የድንቅነሽን ዓጽም አገኙ።
፲፱፻፸፰ ዓ.ም. የግብጽ ወታደራዊ ፈጥኖ ደራሽ ቡድን ተጠልፎ ማልታ ደሴት ላይ ከነመንገደኞቹ በጠላፊዎቹ ቁጥጥር ስር የነበረውን የዓየር ተሽከርካሪ ሲያስለቅቁ ሃምሣ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
፲፱፻፶፮ ዓ.ም. – ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል ተብሎ የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ
- (እንግሊዝኛ) http://lucyexhibition.hmns.org/lucys-discovery.aspx Archived ዲሴምበር 16, 2009 at the Wayback Machine