Jump to content

የሲስተም አሰሪ

ከውክፔዲያ
Ubuntu

የሲስተም አሰሪ (operating system) ተጠቃሚዎችንና ሌሎች በማሽኑ ላይ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን የሚያስተናግድ ፕሮግራም ነው። በዚህ ሥራው የተጠቃሚዎችን ግብአቶች ወይም የማሽኑን ውጤቶችን የሚያቀናብሩ መሳሪያዎችን ይቆጣጠራል፤ የማሽኑን መዝገብ (memory) አጠቃቀም ለሚጠይቁ ፕሮግራሞች ይደለድላል፤ የተለያዩ የማሽኑን የመሳሪያ ሀብቶች (hardware resources) ይደለድላል፤ ማሽኑ ከኮምፒውተር መረብ ጋር ያለውን ግንኙነት ይቆጣጠራል እንዲሁም የመዛግብት (ፋይሎች) አቀማመጥን ያደራጃል።