ድምጽ
Appearance
(ከድምፅ የተዛወረ)
ድምጽ ማለት በአየር፣ በፈሳሽና በጠጣር ነገር ውስጥ የሚጓዝ አየር ጫና ማእበል ነው። ሁሉም በቁስ አካል ውስጥ የሚጓዝ ማእበል ግን ድምጽ አይደለም። ለመሰማት፣ የሚንቀሳቀሰው ሞገድ አንደኛ በቂ ሃይል ሊኖረው ያስፈልጋል (የጩኸቱ መጠን) ፣ የሞገዱ ድግግሞሽ ደግሞ ከ20 ጊዜ በሰከንድ እስከ 20000 ጊዜ በሰከንድ ሲሆን ስምእተ ድምጽ ወይም ለሰው ልጅ የሚሰማው ይሆናል ከ 20000 ጊዜ በሰከንድን ወይም ኸርዝ በላይ ያሉት አልትራ ሶኒክ(አልትራ ሳውንድ) ሲባሉ ከ 20 ጊዜ በሰከንድ (ኸርዝ) በታች ያሉት ሰብ ሶኒክ ይባላሉ ግን እነዚህን ድግግሞሾች የሰው ልጅ ሉሰማቸው አይችልም። የድምጽ መለኪያ አሀዝ ኸርዝ ሲባል የድግግሞሹን መጠን በ አንድ ሰከንድ ይነግረናል።