ጎ
Appearance
ጎ ወይም በቻይንኛ፦ ወይጪ እጅግ ጥንታዊ የሠንጠረዥ አይነት ጨዋታ ነው። በአፈታሪካዊ ልማድ በኋሥያ ንጉሥ ያው ልጁን ዳንዡ ለማስደሰት ተፈጠረ። በሠንጠረዥ 19 x 19 መስመሮች አሉ። የተቃዋሚውን ድንጋዮች በሙሉ በመክበብ ይጠፋሉ (ከሠንጠረዡ ይወገዳሉ።) ከጥንት ጀምሮ በጣም የሚወደድ ጨዋታ ሆኖአል። ዛሬ በተለይም በኢንተርኔት ላይ እጅግ ብዙ የ«ጎ» ድረ ገጾች ይገኛሉ። በነዚህ ድረገጾች ማንም ሰው በኮምፒውተር ላይ ከሌላ ተጫዋች ጋር ወይንም ከኮምፒውተር ተጫዋች ጋር ሊጫወት ይችላል።
-
የጎ ጨዋታ ምሳሌ - መጀመርያ 60 ለውጦች
-
አንድ የኮርያ ባልና ሚስት ከአሁን 100 ዓመት በፊት ጎን ሲጫወቱ