Jump to content

ከውክፔዲያ

(ቻይንኛ፦ 启) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ፪ኛ ንጉሥ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ አባቱ ዳ ዩ ካረፈ በኋላ (2002 ዓክልበ. ግድም) የሦስት ዓመት ልቅሶ ዘመን ተፈጸመ፣ ከዚያ (1999 ዓክልበ. ግድም) ልጁ ጪ ተከተለው። ሲማ ጨን እንደ ጻፈ ግን ዳ ዩ ተከታዩ ጋው ያው እንዲሆን መርጠው ነበር፤ ጋው ያውም አርፎ ተከታዩ የእረኛ (መንጋዎች) ሚኒስትር ቦዪ እንዲሆን ፈለገ። ሕዝቡ ግን ጪን ስለ መረጡ፣ ዙፋኑ ለጪ ተወረሰ።

ቀርቀሃ ዜና መዋዕል፣ በጪ ፪ኛው ዓመት ምኒስትሩ ቦዪ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ ወደ አገሩ ሄደ። ጪ በዚህ ዓመት በዮውሁ ክፍላገር ላይ ዘመተ፣ በጋን ውግያ ተዋጋ። በ፮ኛው ዓመት ቦዪ አረፈ፤ በሌላ ቅጂ ግን ቦዪ ዙፋኑን ለመያዝ አስቦ እንደ ተገደለ ይነግራል። በ፰ኛው ዓመት ጪ ሚኒስትሩን መንግቱን በችሎት ላይ ይቀመጥ ዘንድ ወደ ክፍላገር ላከው። በ፲፩ኛው አመት ጪ ታናሹን ልጅ ዉጓንቢጫው ወንዝ ምዕራብ ወደ ሥሄ አገር አጋዘው። በ፲፬ኛው ዓመት ዉጓን በሥሄ አገር ስለ አመጸ፣ ጪ ከሚኒስትሩ ሾው ሥር አንድ ሥራዊት ልኮ ዉጓን ያንጊዜ እጁን ሰጠ። ከዚያ በኋላ ጪ አርፎ በልጁ ታይ ካንግ ተከተለ።

ቀዳሚው
ዳ ዩ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ ተከታይ
ታይ ካንግ