ነፋስ

ከውክፔዲያ
የነፋስን አቅጣጫና ፍጥነት መለኪያ አኔሞሜትር

ነፋስ ሁለት አይነት ትርጉሞች አሉት። በመሬት ላይ፣ ንፋስ የሚባለው የአየር እንቅስቃሴ ነው። ከመሬት ውጭ ባለው ጠፈር ንፋስ የሚባለው የአየር ወይንም የተለያዩ እኑሶችን እንቅስቃሴ ነው። ለምሳሌ ከፀሐይ ፈንድተውና ተስፈናጥረው ወደ ጥልቁ ኅዋ የሚጓዙት እኑሶች ፀሐያዊ ነፋስን ይፈጥራሉ። በፀሐይ ሥርአተ ፈለክ(ፕላኔት) ውስጥ ከፍተኛ ነፋስ የሚነፍስባቸው ኔፕትዩንሳተርን ናቸው።

ነፋስ እንደ ሃይሉና የሚውስደው ጊዜ እንዲሁም እንደ እርጥበቱ ይከፈላል፡፡ ከክፍሎቹም ውስጥ

የነፋስ ተፈጥሮ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አንድሩ አውሎ ንፋስ የፈጠረው ጥፋት

በመሬት ላይ የሚፈጠሩ ነፋሶች ምክናያታቸው የአየር ጫና ልዩነት ነው። በሁለት አካባቢዎች መካከል የተለያየ የአየር ጫና ሲኖር፣ ልዩነቱ እስኪጠፋ ድረስ አየር ክከፍተኛ ጫና ወደ ዝቅተኛ ጫና ይሰደዳል። በሚሰደድበት ውቅት ነፋስን ይፈጥራል። ሞቃታማ የአየር ክፍል ከቀዝቃዛ የአየር ክፍል ያነሰ ጫና ስላለበት ብዙ ጊዜ ነፋስ የሚነፍሰው ከቀዝቃዛ ክፍል ወደ ሞቃታማ ክፍል ነው። ስለሆነም ነፋስ ብዙ ጊዜ ቀዝቃዛ ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ በቋሚነት ለሚነፍሱ ነፋሶች ተጠያቂዎቹ ሁለት ምክንያቶች ናቸው። አንደኛው በምድር ወግብ እና በምድር ዋልታዎች መካከል ያለው የሙቀት ልዩነት ሲሆን ሁለተኛው የመሬት በራሷ ዛቢያ ላይ መሽከርክር ነው።

አንስተኛ የአየር ጫና ልዩነት ባለባቸው አካባቢዎች ለምለም ነፋስ ወይን ቀሰስተኛ ነፋስ ይፈጠራል። ሆኖም ከፍተኛ ልዩነት ባለባቸው አካባቢዎች እስከ 200 ማይል በሰዓት የሚጓዝ እጅግ ፈጣን አውሎ ነፋስ ይፈጠራል። በዚህ ፍጥነት የሚጓዝ ነፋስ ቤቶችን እስከማፍረስ እና ህይወት እስከማጥፋት ሃይል ይኖረዋል።

ነፋስ ኃይል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህ የነፋስ እሽክርክሪት ነፋስን በመጠቀም ኤሌክትሪክ ያመነጫል

በታሪክ አንጻር የስሪ ላንካ ሰዎች፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት 300 ዓ.ዓ. ጀምረው የንፋስን ሃይል ሙቀት ለመፍጠርና ብረትን ለማቅለጥ እንደተጠቀሙበት ይጠቀሳል[1]። እኒህ ምድጃዎች በሞንሱን ነፋስ መንገድ ላይ የሚነቡ የነበር ሲሆን የሚፈጥሩት ሙቀት እስከ 1200 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ይደርስ ነበር። ከሺህ አመት በኋላ የመጀመሪያው በሥራ ላይ የዋለ የነፋስ ወፍጮ አፍጋኒስታን ውስጥ በ7ኛው ክፍለ ዘመን (ከክርስቶስ ልደት በኋላ) እንደተሰራ ይጠቀሳል። [2] የኒህ ወፍጮዎች ጥቅም እህልን ለመፍጨትና ውሃን ከጉድጓድ ለማውጣት ነበር።[3] ከ1170ዎቹ ጀምሮ በሰሜን-ምዕራብ አውሮጳ ክፍሎች የነፋስ ወፍጮወች በሰፊው ጥቅም ላይ መዋል ጀመሩ።

በአሁኑ ወቅት የነፋስ ኤሌክትሪክ ማመንጫውች በአለም ላይ እየተሰራጩ ሲሆን አቅዳቸውም ከድሮዎቹ የነፋስ ወፍጮወች ይመነጫል። ከመሬት እየተራቀ በሄደ ቁጥር የነፋስ ፍጥነት እየጨመረና አስተማማኝም እየሆነ ስለሚመጣ ብዙ ኩባንያዎች ከከባቢው አየር በጣም ከፍ ብሎ ያለውን ነፋስ ለኤሌክትሪክ ምንጨታ ስራ እንዴት እንደሚያውሉት እያጠኑ ይገኛሉ። ጥናቱ ስኬት ካመጣ የአለምን የሃይል ፍላጎት በዚህ መንገድ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት ይቻላል[4]

አውሎ ንፋስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአውሎ ንፋስ ዓይነቶች በፉጂታ መለኪያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መለኪያ የንፋስ ፍጥነት ተደጋግሞ የመከሰቱ መጠን ሊያደርሰው የሚችለው የጥፋት አይነት
ማይልስ በሰዓትmph ኪሎሜትር በሰዓትkm/h
EF0 65–85 105–137 53.5% አንስተኛ ወይንም ምንም ጥፋት

በአሸንዳ ላይ ትንሽ ጉዳት፣ ከጣሪያ ላይ ትንሽ ነቅሎ መውሰድ፣ የዛፎች ቅርንጫፎች መሰበር፣ ጥልቅ ስር የሌላቸው ዛፎች ተገፍተው ይወድቃሉ

EF0 ለምሳሌ የሚያደርሰው ጥፋት
EF0 ለምሳሌ የሚያደርሰው ጥፋት
EF1 86–110 138–178 31.6% መካከለኛ ጥፋት

ጣሪያዎች በሃይል ይገለባሉ፣ ተንቀሳቃሽ ቤቶች ይገለበጣሉ፣ የውጭ በሮች ይገነጠላሉ፣ መስኮት እና ሌሎች መስታወቶች ይሰበራሉ

EF1 ለምሳሌ የሚያደርሰው ጥፋት
EF1 ለምሳሌ የሚያደርሰው ጥፋት
EF2 111–135 179–218 10.7% ከበድ ያለ ጥፋት

በደምብ ከተሰሩ ቤቶች ላይ ጣሪያወች ተገንጥለው ይሄዳሉ፣ የፍሬም ቤቶች መሰረት ይናወጣል፣ ተንቀሳቃሽ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ይወድማሉ፣ ትላልቅ ዛፎች ይቀስፋሉ፣ ወይንም ከስራቸው ይመነገላሉ፣ ተስፈንጣሪ አደጋ ጣይ እቃዎች በአየር ውስጥ የፈጠራሉ፣ መኪናዎች ከመሬት ይነሳሉ

EF2 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF2 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF3 136–165 219–266 3.4% ከባድ ጥፋት

በጥሩ ሁኔታ የተሰሩ ቤቶች ይፈርሳሉ፣ ትላልቅ ፎቆችና እና ህንጻዎች፣ ሞሎች፣ ከፍተኛ አደጋ ይደርስባቸዋል፣ ባቡሮች ይገለበጣሉ፣ ዛፎች ከቅርፊታቸው ይላቀቃሉ፣ ከባባድ መኪናዎች ከመሬት ተነስተው ይወረወራሉ፣

EF3 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF3 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF4 166–200 267–322 0.7% ከፍተኛ ጥፋት

በደምብ የተሰሩና ሙሉ ፍሬም ያላቸው ቤቶች ሙሉ በሙሉ ይወድማሉ፣ መኪኖችና ሌሎች ትላልቅ ነገሮች ይወረወራሉ፣ ትናንሽ ሚሳኤሎች ይፈጠራሉ፡

EF4 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF4 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF5 >200 >322 <0.1% ሙሉ በሙሉ ውድመት

ጠንካራ ፍሬም ያላቸውና በጥሩ ሁኔታ የተሰሩ ቤቶች ይወድማሉ፣ መሰረታቸው ተጠርጎ ይጠፋል፣ በፌሮ የጠነከሩ የኮንክሪት ቤቶችና ግንቦች በሃይል ይጎዳሉ፣ ረጃጅም ህንጻዎች ይፈርሳሉ፣ ወይንም ከፍተኛ መዋቅራዊ ጉዳት ይደርስባቸውል።

EF5 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ
EF5 ከሚያደርሰው ጥፋት ምሳሌ

ተጨማሪ ንባቦች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ G. Juleff (January 1996). An ancient wind powered iron smelting technology in Sri Lanka. pp. 60–63. 
  2. ^ Ahmad Y Hassan and Donald Routledge Hill (1986). Islamic Technology: An illustrated history. Cambridge University Press. p. 54. ISBN 0-521-42239-6. 
  3. ^ Donald Routledge Hill (May 1991). Mechanical Engineering in the Medieval Near East. pp. 64–69. 
  4. ^ Dietrich Lohrmann (1995). Von der östlichen zur westlichen Windmühle. pp. 1–30.