አውራሪስ

ከውክፔዲያ
?አውራሪስ
ጥቁር አቅራሪስ, Diceros bicornis
ጥቁር አቅራሪስ, Diceros bicornis
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ጐደሎ ጣት ሸሆኔ Perissodactyla
አስተኔ: አውራሪስ Rhinocerotidae
Gray, 1821

የቤተሰቡ የተለያዩ አባላት

Ceratotherium
Dicerorhinus
Diceros
Rhinoceros
Coelodonta (extinct)
Elasmotherium (extinct)

አውራሪስ ተብሎ የሚታውቀው አጥቢ የዱር አራዊት አምስት የተለያዩ የዘር አይነቶች አካቶ ሲይዝ በባዮሎጂ ባለሞያዎች ጐደሎ ጣት ሸሆኔ ተብለው ከሚታወቁት ቀንዳማ እንስሶች አንዱ ነው። እነዚህ አምስቱም የአውራሪስ አይነቶች በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ)፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በደቡብ እስያ ይገኛሉ። ከነሱም መሃል አብዛኞቹ ሊጠፉ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ።

ቃሉ አውራሪስ የወጣው ከግዕዝ አርዌ ሀሪሥ ማለት «ባለ-ቀንድ አውሬ» ነው።