ዋይት ሃውስ

ከውክፔዲያ
የኋይት ሃውስ ደቡባዊ ገፅ

ኋይት ሃውስአሜሪካ ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የመኖሪያ እና መደበኛ የስራ ቦታ ነው። ይህ ቤት የተገነባው ከ1792 እስከ 1800 እ.ኤ.አ. ባሉት አመታት ሲሆን የገነባውም የአየርላንድ ተወላጅ በሆነው አርኪቴክት ጀምስ ሆባን (James Hoban) ነበር። ቤቱ ከጆን አዳምስ (John Adams) ጀምሮ ለሁሉም የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች መኖሪያ የሆነ ሲሆን ቶማስ ጄፈርሰን (Thomas Jefferson) የተባለው የአሜሪካ 3ኛ ፕሬዝዳንት በ1801 ሲገባ በአርኪቴክት ቤንጃሚን ሄንሪ ላትሮብ (Benjamin Henry Latrobe) ቤቱን ወደውጭ አስፍቶታል።