Jump to content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

ከውክፔዲያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክመጋቢት ፪ ቀን ፲፰፻፺፯ ዓ/ም የተመሠረተ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ባንክ ነው። ባንኩ ሲመሠረት የተሰጠው ስያሜ «የአበሻ ባንክ» (እንግሊዝኛ፡ Bank of Abyssinia) ሲሆን የመጀመሪያ ቅርንጫፉ በዚሁ ዕለት በዳግማዊ ምኒልክ ተመርቆ ለአገልግሎት ሲቀርብ የባንኩ መንቀሳቀሻ ንብረት (capital) አምሥት-መቶ ሺህ የእንግሊዝ ፓውንድ ነበር።[1] መቀመጫው በዋና ከተማአዲስ አበባ ውስጥ ይገኛል። የዚህ ባንክ ስም በምህጻረ ቃል ኢብባ ወይም ENB ነው። ዋና አስተዳዳሪው አቶ ንዋየ ክርስቶስ ገብረ አብ ናቸው። በዋነኛነት የሚጠቀመው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር ነው ሲሆን መሰረታዊ የማበደሪያ ወለዱ ስምንት በመቶ (8%) ነው። በአንጻሩ የማስቀመጫ ወለዱ ደግሞ ሦስት በመቶ (3%) ነው።

ዋቢ ምንጮች እና ማገናዘቢያዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2013-10-21. በ2013-09-09 የተወሰደ.