ጉግል

ከውክፔዲያ
ኢንዱስትሪ ኢንተርኔት
ገቢ $6.138 ቢሊዮን (2005 እ.ኤ.አ.)
ቅርንጫፎች {{{ድህረገፅ}}}


ጉግል (Google)1998 እ.ኤ.አ. የግለሰብ ድርጅት ሆኖ ነው የጀመረው። የጉግል ፍለጋ ዌብሳይትን የሰራው እና የሚያስተዳድረው ይሄው ድርጅት ነው። የጉግል ዓላማ የዓለምን መረጃ ለማሰናዳት ፣ ለማቅረብና ጠቃሚ ማድረግ ነው።



ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መጀመሪያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጉግል እንደ ፕሮጀክት ሆኖ በጃኑዋሪ 1996 እ.ኤ.አ.ላሪ ፔጅ እና ሰርጂ ብሪንስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ነው የጀመረው። የፕሮጀክቱ ሀሳብ የድረ ገጾችን ግንኙነት በማጥናት የተሻለ የፍለጋ አገልግሎት መሰጠት መቻል ነበር። ወደ አንድ ድረ ገጽ ብዙ መያያዣዎች ካሉ ያ ድረ ገጽ ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን አለው የሚለውን ሀሳብ ሞክረው ትክክለኛ መሆኑን አዩ (ይህ ዘዴ ፔጅራንክ ይባላል)፣ ለፍለጋ ድረ ገጻቸውም መሠረት ጣሉ። በእዚያ ጊዜ ፍለጋውን የሚያስተናግደው የስታንፎርድ ዌብሳይት ነበር። አድራሻውም http://google.stanford.edu ነበር። ያሁኑ አድራሻቸው google.com በመስከረም 5 ቀን, 1990 (Sep. 15, 1997 እ.ኤ.አ.) ነው የተመዘገበው።

የጉግል ዌብሳይት

በማርች 1999 እ.ኤ.አ. ድርጅቱ ወደ 165 ዩኒቨርስቲ አቬኑ, ፓሎ አልቶ መስሪያ ቤቱን አዛወረ። ከዚያ በኋላ ሌሎች ሁለት ቦታዎች ቢቀያይሩም በ2003 እ.ኤ.አ. 1600 አምፊቲያትር ፓርክዌይ, ማውንቴን ቪው ወደ ሚገኙ ሕንጻዎች አረፉ። አብዛኛው በዚህ ጊዜ ይጠቀምበት የነበረው የኮምፒዩተር ዕቃዎች ከኢንቴል እና አይቢኤም የተለገሡ ነበሩ።

በፍጥነት የሚያድገው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ጉግልን ማድነቅ ጀመሩ። ተጠዋሚዎች ወደ ዌብሳይቱ ቀላል እና ዓይን የሚስብ ዲዛይን ተሳቡ። በ2000 እ.ኤ.አ. በፍለጋ ቃላት ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ጀመሩ። ነጻ የዌብሳይት ዲዛይን አንዲኖርና የዌብሳይቱን የመጫን ጊዜ ፈጣን እንዲሆን ማስታወቂያዎቹ የምስል ሳይሆን የጽሁፍ ብቻ ናቸው። ሌሎች ተወዳዳሪዎቹ እየወደቁ ሲመጡ ጉግል ግን እያደገ እና እየታወቀ መጣ።

ነሐሴ 29 ቀን, 1993 (Sep. 4, 2001 እ.ኤ.አ.) የዩናይትድ ስቴትስ ፓተንት ቢሮ የፔጅራንክ ዘዴን ፓተንት ለስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሰጠ። በፌብሩዋሪ 2003 እ.ኤ.አ. ጉግል ፓይራ ላብስ የሚባለውን የብሎገር ባለቤት ገዛ።

2004 እ.ኤ.አ. መጀመሪያ ጉግል በወርልድ ዋይድ ዌብ ከነበረው የፍለጋ ጥያቄዎች 84.7 በመቶውን በራሱ ዌብሳይትና በሌሎች ጓደኛ ዌብሳይቶች ያስተናግድ ነበር። በፌብሩዋሪ 2004 እ.ኤ.አ. ያሁ! ከጉግል ጋር የነበረውን ጓደኝነት አቆመ።

በበዓል ቀናት፣ የአንድ ነገር መታሰቢያ ቀናት እና ልዩ ቀኖች የጉግል ዌብሳይት አስቂኝ ነገሮችን ይይዛል። ከነዚህም ታዋቂው የድርጅቱን አርማ መለወጥ ነው። ይህም 'ጉግል ዱድልስ' ይባላል።

በየጊዜው አዲስ ነገር ከጉግል ይመነጫል። ጉግል ላብስ የሚባለው የዌብሳይቱ ክፍል አዲስ በሙከራ ያሉ ውጤቶችን ይይዛል። ይህም የተጠቃሚዎችን አስተያየት ስለሚያስገኘው ከተጠቃሚዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ያዳብራል። ይህም አዲሶቹን ምርቶች አሰራር ያሻሽላል።

የአርማ ለውጥ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዓመታት ውስጥ የጉግል አርማ ተለውጧል።

የቃል አመሠራረት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጉግል (Google) የሚለው ቃል ጉጎል (Googol) ከሚለው የመጣ ነው። ጉጎል የሚባለው ቃል የተፈጠረው በሚልተን ሲሮታ1938 እ.ኤ.አ. በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ሚልተን ኤድዋርድ ካስነር የሚባል ማቲማቲሻን ወንድም/እሀት? ልጅ ነው። የቃሉ አጠቃቀም የጉግልን በኢንተርኔት የሚገኘውን ኢንፎርሜሽን ለማሰናዳት ያለውን ዓላማ ያንፀባራቃል። የጉግል ጠቃላይ መምሪያ ጉግልፕሊክስ (Googleplex) ይባላል።

ዛሬ 'ጉግል' በአንዳንድ ቋንቋዎች እንደ ቃል ይወሰዳል። ትርጉሙም 'የዌብሳይት ፍለጋ ማድረግ' ነው።

ፋይናንስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጉግል የመጀመሪያ ዕርዳታ ከአንዲ ቤክቶልሸም የተጻፈ የ$100,000 ቼክ ነው።

ዛሬ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጉግል እያደገ ሲመጣ ትልቅ ውድድር እየሳበ ይመጣል። አንድ ምሳሌ በጉግል እና ማይክሮሶፍት መሀል ነው። ማይክሮሶፍት ኤምኤስኤን ሰርች የሚባለውን የፍለጋ አገልግሎት በየጊዜው እየለወጠ ከጉግል ጋር የተወዳዳሪ ቦታ እንዲይዝ ይሞክራል። ከዚህም በላይ ሁለቱ ድርጅቶች አንድአይነት አገልግሎቶችን ማቅረብ ጀምረዋል።

ጉግል በፍለጋ አገልግሎት መሪ ስለሆነ እንደ ያሁ! ያሉትን ተወዳዳሪዎች ለማሸነፍ ይጥራል። የጉግልና ያሁ ትኩረት የተለያየ ቢሆንም ጉግል ግን አዳዲስ አገልግሎቶችን እየከፈተ ነው። በጁን 21, 2005 እ.ኤ.አ. ጉግል እንደ ኢቤይ ያሉትን የንግድ ዌብሳይቶችን ለመወዳደር ያለውን ዕቅድ አሳውቋል።

ሠራተኞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በጉግል የመጀመሪያ ዓመታት የሠራተኞች ደሞዝ ትንሽ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ግን ዩጉግል ሼር በከፍተኛ መጠን እያደገ ስለመጣ የሠራተኞች ደሞዝ በአንጻሩ ጨምሯል። ከደሞዝ ሌላ ታዋቂነት እና ሌሎች ጥቅሞች ብዙ አመልካቾችን ስቧል። ከአንድ ላነሰ የሥራ ቦታ አንድ ሺህ አመልካቾች እንዳሉ ተገምቷል።

የድርጅቱ መሥራቾችና ሌሎች ዋና ሠራተኞች አንድ የአሜሪካን ዶላር እየተከፈላቸው ይሰራሉ። እነዚህ ሰዎች የድርጅቱን ብዙ ሼር ይይዛሉ። ማርች 31 2007 የተለቀቀው መረጃ እንደሚያመለክተው ጉግል 12238 ሰራተኞች አሉት።

ቴክኖሎጂ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጉግል አገልግሎቶች በብዙ ሰርቨሮች ውስጥ በሚገኙ ተራ ኮምፕዩተሮች ላይ ነው ያሉት። ኮምፒዩተሮቹ የሊኑክስ ኮምፒዩተር ፕሮግራም ይጠቀማሉ። ድርጀቱ ስለሚጠቀመው ማሽኖች ብዙ ዝርዝር ባይሰጥም በ1996 ከ60,000 በላይ ኮምፒዩተሮችን እንደሚጠቀሙ ይገመታል።

ፔጅራንክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፔጅራንክ (PageRank) ጉግል የፍለጋ ገጾቹ ላይ የዌብሳይቶችን ቅድመተከተል ለማግኘት የሚጠቀመው ዘዴ ነው። በፔጅራንክ እያንዳንዱ ዌብሳይት ቁጥር አለው። ይህ ቁጥር ከፍ ባለ ጊዜ የዛ ዌብሳይት ደረጃ በፍለጋ ገጹ ላይ ይጨምራል። ይሄ ቁጥር የሚወሰነው ሌሎች ወደዚህ ዌብሳይት በሚያመለክቱ ዌብሳይቶች ነው። የእነዚህ ዌብሳይቶች ቁጥር ከፍተኛ ከሆነ የዚኛውም በአንጻሩ ይጨምራል። በኣንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ ይህ ኣስተማማኝ ላይሆን ይችላል።

የድርጅቱ ባሕል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ፍልስፍና[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጉግል የራሱ የተለያዩ ዕምነቶች አሉት። አንዱ 'መጥፎ ነገር ሳትሰራ ገንዘብ ማግኘት ትችላለህ' ይላል። ሊሎች ዋና ሀሳቦች እዚህ ይገኛሉ

'ሃያ በመቶ' ጊዜ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሁሉም የጉግል ኢንጅነሮች 20 በመቶ የሥራ ጊዜያቸውን እነሱ በሚስባቸው ሥራ ላይ እንዲያሳልፉ ያበረታታል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንድ ሥራዎች የጉግል ሌላ አገልግሎት ይሆናሉ።

ጉግልፕሌክስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጉግል መጥላይ መምሪያ ጉግልፕሌክስ (Googleplex) ይባላል። ይህ ቦታ ለሠራተኞች የተለያዩ መዝናኛዎችን ያቀፈ ነው። ከነዚህም ውስጥ የአካል ማጎልመሻ ክፍል፣ የተለያዩ ስፖርቶች፣ የተለያዩ ምግብና መጠጦች ይጠቀሳሉ።

የስራ ትብብር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሚከተሉት የሥራ አጋሮች ናቸው፦

ዓለምአቀፍ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጉግል ከደርዘን በላይ በሚሆኑ ሀገሮች ቢሮዎች አሉት። የተለያዩ ሀገሮች የተለያየ ሕጎች ስላሏቸው ጉግል ሁሉንም ለማስማማት ይሞክራል።

የፍለጋ ዓይነቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ምስሎች (Images) - ይህ በኢንተርኔት ላይ ያሉ ምስሎችን ብቻ ለመፈለግ ያገለግላል
  • የውይይት መድረኮች(Groups) - የመወያያ ግሩፖችን ለመፈለግ
  • ዜና (News) - ከተለያዩ ምንጮች ዜናን ለማንበብ
  • ፕሮዳክት ፍለጋ (Product Search) (የድሮ "ፍሩግል" Froogle) - ይህ ድረ-ገጽ ተጠቃሚዎች በኢንተርኔት ዕቃ እንዲገዙ ያስችላል። ፍሩግልን ይዩ
  • ሎካል (Local) - በአቅራቢያዎ ያሉ ሱቆችንና ሌሎች የንግድ ቦታዎችን ለመፈለግ ያገለግላል
  • እርዝ (Earth) - የዓለም የሳይተላይት ፎቶዎችን የሚያሳይ ፕሮግራም ወደ ኮምፒዩተሮ መጫን ይችላል
  • ዴስክቶፕ (Desktop) - በኮምፒዩተሮ ላይ ያሉትን ሰነዶች (ፅሁፍ፣ ፎቶ፣ ድምፅ፣ ምስል) ለመፈለግ
  • ቪዲዮስ (Videos) - በኢንተርኔት ላይ ያሉ ቪዲዮችን ለመፈለግ
  • ብሎግስ (Blogs) - በኢንተርኔት ላይ ያሉ ብሎጎችን ለመፈለግ
  • ስኮላር (Scholar) - ትምህርታዊ ጽሁፎችን ለመፈለግ
  • ፋይናንስ (Finance) - የንግድ መረጃ፣ ዜና እና ሰንጠረዦች ለመፈለግ
  • ካርታ (Maps) - ካርታዎችንና የመንጃ መመሪያዎችን ለማየት

የውጭ መያያዣዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]