ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም
Appearance
ግሸን ደብረ ከርቤ | |
ምዕመናን ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ሲጓዙ | |
ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በአሁኑ ወሎ ዞን፣ አምባሰል ወረዳ ውስጥ ግሸን ተራራ አናት ላይ የምትገኝ ቤ/ክርስቲያን ናት። ለዚች ቤ/ክርስቲያን መግቢያ አንድ መንገድ ብቻ ነው። እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይች ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ የተለያየ ስያሜን አግኝታለች።
- ከአጼ ድልናአድ ዘመን (866 ዓ.ል) እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን በአሁኑ ስያሜ (ደብረ ከርቤ) ትታወቅ ነበር።
- በ11ኛው ክፍለ ዘመን አጼ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍለው እግዚአብሔር አብ የተሰኘ ቤ/ክርስቲያን በዚሁ ቦታ ሲያሰሩ ደብረ እግዜአብሔር በሚል ስም ታወቅፕች። ብዙ ሳይቆይ ግን ደብረ ነገስት ተባለች።
- በ1446 አጼ ዘርአ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን በዚህ ስፍራ ሲያርፍ ደብረ ነገስት መባሏ ቀርቶ ደብረ ከርቤ ተባለች። በዚህ ጊዜ የነበረው የቤ/ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መምህረ እስራኤል ዘ ደብረ ከርቤ ይባል ነበር።
- አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ይዘው እየገሰገስገሱ ስለመጡ በግዕዙ "ገሰ" ወይም በአማርኛው "ገሰገሰ" የሚለው ቃል ለቦታው ስያሜ ሆነ። በዘመናት ሂደት ገስ ወደ ግሸን የሚለው ስያሜ ተዛወረ። አካባቢው በዚህ ስም ታወቀ።
እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊት፣ የግሸንን ደብር የመሰረታት አንድ ጻድቅ መነኩሴ ነበር። ይኽውም በ514 ዓ.ም፣ ከዘርዓ ያዕቆብ መነሳት 900 አመት በፊት ነበር። የሆኖ ሆኖ አካባቢው በአሁኑ ዘመን የሚታውቀው የኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል በማኖሩ ነው። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በነገሱ ዘመን ወደ ፉንግ ስናር ሄደው ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤ/ክርስቲያን ውድ ንዋያትን አምጥተው መስከርም 21፣ 1446 ዓ.ም ወደ ደብሩ በመውጣት በዘመኑ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት እንደገና በማነጽ፤ በኋላም በእግዚአብሔር አብ ቤ/ክርስቲያን ጥግ በጥንቃቄ ጉድጓድ አስቆፍረው መስቀሉን በማስቀበርና ባለቤታቸው ንግስት እሌኒ ደብረ ከርቤ ማርያም ቤ/ክርስቲያንን እንደገና በማሳነጽ ከፍተኛ ስራ አከናወኑ። ከ5 አመት በኋላ መስከርም 21፣ 1449 ጀምሮ የመስቀል በዓል በዚህ ዕለት መከበር ተጀመረ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |