ሀይሉ ወርቁ

ከውክፔዲያ

ሀይሉ ወርቁኢትዮጵያ ስነፅሑፍ ራሱን በራሱ ስነፅሑፍን በማስተማር ከአስር በላይ መፅሐፍትን የፃፈ ደራሲ ነው። በሦስት ቋንቋም ይፅፋል።


ደራሲው ሐይሉ ወርቁ የአስራ አንድ መጽሐፍት ደራሲ፥

  1. ላለፉት አስር ዓመታት በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥናት አድርጎ ከአስር ባላይ መፅሐፍትን የፃፈ፣
  2. በበርካታ አገራዊ ጥናቶች ላይ የተሳተፈ፣
  3. የመጀመሪያው የአማርኛ ቃላት መሰብሰብ ፕሮጅክት የመራ እና እየሰራ ያለ፣
  4. የውጪ ሐይሎች በኢትዮጵያ የሚሰሩትን የዳርስቶጵያ ፕሮጀክትን በጥናት በተደገፈ ሰነድ ያዘጋጀ እና በዚሁ ጥናት ላይ ተመስርቶም የፓቶጵያ ፍቅር የተሰኘ መፅሐፍ የፃፈ፣
  5. የፒ.ኤች.ዲ ትምህርቱን እየተማረ ያለ ለአገር እና ለወገን ተቆርቋሪ፣ በሥራው ታታሪ ሰው ነው።


ሞት በውክልና[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

hailu worku
ሞት በውክልና

የመፅሐፊ አጠቃላይ ሁኔታ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሞት በውክልናመፅሐፍ ታሪክ ግጥም የተገጥመለት፣ ዘፈን የተዘፈነለት ድንቅ ታሪክ ነው። ሞት በውክልና በፍቅር ዘውግ የተፃፈ መፅሐፍ ሲሆን ፥ ልብን ትርክክ አድርጎ፣ አኧምሮን በማመራመር ፤ አንጀት የሚያላውስ ድንቅ የፍቅር ታሪክ ላይ የተፃፈ ነው ታሪካዊ መፅሐፍ ነው። ይህ ታሪክ በታገል ሰይፉ ተፅፎ፣ በሀይለየሱስ ግርማ ዜማ ስላዜመለት ሰው ታሪክ ብቻ አይደለም። ያ ሚስኪን ሰው ስላፈቀራት እና በስተመጨረሻ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፤ ለሦስተኛ ጊዜ ሞተች ተብሎ ዕድርተኛው ቀብሩን ሊቀብር፣ በእአባቷ ግቢ ቢሰበሰብም፤ እሷ ግን ዛሬም እንደ ባለፈው መሞት አቅቷት ክፉኛ ተሰቃይታ፤ ቤተሰቡን እያሰቃየች ስለነበረች እና መሞት አቅቷት በጣዕረ ሞት ከተያዘች እነሆ ዛሬ ዘጠና አራተኛ ስላስቆጠረች ልዩ ሴት ነው።

ይህን ባለ 256 ገፅ የሆነው መፅሐፍ፥ የአርታኦት ሥራው የሰራው ታዋቂው አርታኢ እና የፊልም ተዋናይ፣ የአማርኛ ቋንቋና ሥነጽሑፍ ምሩቅ ዳዊት (ዴቮ) ነው።

ገፀባህሪያቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አንድ ሰው ነበረ፤ የተለየ ልብ ያለው። አኧምሮውን ማዘዝ እና ማስቆም የሚችል ልብ። አኧምሮው ሲያስቆመው አካሉም እዛው ተገተረ። ያለ ተስፋ፣ ያለረዳት፣ እዛው እንድቆመ ፤ ለምን እንደሆነ ባላወቀው ምክንያት፣ ሁሉም ነገር በዙሪያው በፍጥነት ይለዋወጥ ነበር። ለተመለከተው ፊቱ ይናገራል፣ እሱ ለውጡ አልገባውም። እዛው በመንገዱ ዳር እንደቆመ መልኩ ጠፉ፣ ውበቱ ረገፈ። ዓመታት አለፉ። መንገደኛው ሁሉ ይህ ሰው ብቸኛ ነው ብሎ ያዝናል። እሱ ግን ለምን እንደታዘነለት፣ ነገሮችም ሁሉ እየተለወጡ መሆናቸውን አያውቅም። በዚያች ቦታ ለዓመታት ከመቆሙ የተንሳ፣ እርሱ የቦታው ምልክት ሆኗል። ሰው ሁሉ ቦታውን ለመለየት የተለየ ሥዕሎች እና ማስታወቂያ አላስፈልገውም። ሰዎች እሱን እዚያ ቦታ ላይ ለሲሶ ምዕተ ዓመት ያህል ዘመን የገተረው ጉዳይ ምን እንደሆነ አያውቁትም፣ ቢያውቁትም አይገባቸውም። ምክንያቱም ሰዎች ሁሉ እሱ ያለው ዓይነት ልብ የላቸውም ! ይህ መፅሐፍ ግን ስለእርሱ ሳይሆን፤ እርሱ ስለሚያውቃት፣ እና መኖርም መሞትም አቅቷት ስለምትሰቃይ ቤተልሔም ስለተባለች ሴት እንጂ። ሁሉም ገፀባህሪያት የየራሳቸው ቀለም አላቸው። ሞትን ለዘጠና አራት ቀናት የተዋጉትን ቀስ አገኘውን፣ ሰላቢዋ ፅጌ፣ ቀላብላባዋ ወ/ሮ ማንጠግቦሽ፣ የሰውን ሚስት ይዞ አሜሪካ በመግባት፣ ሰውን 32 ዓመታት መንገድ ላይ የገተረውን ይሀይስን …. ብቻ ሁሉንም ማንም መርሳት አይችል።

አፃፃፉ ዘይቤ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በልማዱ የልብ ወለድ ድርሰት ደራሲዎች ከፍ ወይም ዝቅ ብለው የሚገመቱት ለድርሰታቸው የሚፈጥሩት ታሪክ፣ ላንባቢዎች በሚሰጠው ትምህርት እና ታሪኩን በጥሩ አጻጻፍ አስጊጦ ለማቅረብ ባላቸው ችሎታ ነው። ላንባቢዎች አኧምሮ ትምርትን፣ ለልባቸው ደስታን የሚሰጥ ልብ ወለድ ድርሰት ጥሩ ድርሰት ይባላል። እንዲህ ላሉ ድርሰቶች ደራሲዎችም ትልቅ ደራሲዎች ይባላሉ። እኔ ይህች “ሞት በውክልና” ብዬ ሰይሜ ላንባቢዎች የማበረክታት ልብ ወለድ ድርሰት በታሪክዋም ሆነ ባጻጻፍዋ ጥሩ ድርሰቶች የሚባሉት በያዙት ደረጃ እንኩዋንስ ልትደርስ እንደማትቀርብ አውቃለሁ። ነገር ግን ብዙ ጥሩ ድርሰቶች ያልያዙት መልክት ላንባቢዎች ለማድረስ የተሰናዳች ስለሆነችና በተለይ የኢትዮጵያን አንባቢዎች ለሚያሳስቡ እስከ ዛሬ ድረስ መልስ ላላገኙ አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ ሊሆኑ የሚችሉ አሳቦች ይዛ ስለምትቀርብ አንባቢዎች ሳይሰለቹ በማስተዋል እንዲመለከቱልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ዲሳንግዌ
የወታደሩ ሚስት
የእንጠጦ ደራሲ
የዴልታው ልዕልት
ከሁሉም በላይ ደራሲው የሚወደው መጽሐፉ ነው።

ሌሎች የደራሲው ሥራዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. በማስተዋል ወደ ባለጠኘት ማደግ
  2. የፓቶጵያ ፍቅር
  3. ሶፕራለ
  4. ምናሴ መናጢው እና የኢትዮጵያ መምህራን
  5. አይኮ
  6. ዕብዱ አጥናፉ ወርቁ

</gallery>

  1. ዕጸ ሐበቅ እና ጭራ አልባዎቹ
  2. የነፍስ እናት እና ልጇ
  3. የዴልታው ጌታ
  4. የሁፐስ ፍቅር
  5. የጠፏ የአዲስ አበባ ሴቶች
  6. ዲ ሳንግዌ
  7. የመጨረሻው ወታደር ልጅ እና ሌሎች