Jump to content

ሂርካኒያ

ከውክፔዲያ
የሂርካኒያ ስፋት

ሂርካኒያ በጥንታዊ ፋርስ አገር የነበረ አውራጃና ግዛት ነበር። በ523 ዓክልበ. በገደል የተቀረጸው የቤኂስቱን ጽሑፍጥንታዊ ፋርስኛ «ቬርካና» ይለዋል፤ ይህ የተኲላ (ቬርካ) አገር ማለት ነው። ሂርካኒያ ከ530 እስከ 337 ዓክልበ. ድረስ የፋርስ መንግሥት ክፍላገር ሲሆን ከታላቁ እስክንደር በኋላ እስከ 200 ዓክልበ. ግድም ድረስ ግሪኮች አስተዳደሩት። ከዚያ እስከ 200 ዓ.ም. ድረስ የጳርቴ ሰዎች አስተዳደሩት፣ ከነርሱም በኋላ የሳሳኒድ መንግሥት ክፍል ነበር። የሳሳኒድ መንግሥት በ641 ዓ.ም. ለእስላሞች ኃያላት በወደቀበት ዘመን፣ የዞራስተር ተከታዮች ቅሬታ በሂርካኒያ እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ድረስ በነጻነት ቆመ።