ሃድጎ -አህያ ሸራህያ
Appearance
ጋዜጠኛው አረፋይኔ ሀጎስ ስለ አለቃ ገብረ ሃና መጽሀፍ ጽፏል። ታዲያ አለቃ ከአጼ ተዎድሮስ ጊዜ ጀመሮ የነበሩ የቤተክርስቲያን ምሁር እንደሆኑ ነው መጽሀፉ የሚያወራው። ከጊዜው ቀልዳቸው አንዱ እንዲህ ይላል። በአጼ ተዎድሮስ ቤተመንግስት ሀድጎ የሚባል ባለሟል ነበረ ታዲያ ምንም እንኳን ንጉሱ ቀልድ የማያውቁ ኮስታራ ቢሆኑም አለቃ ግን መኮመኪያ ምክንያት አላጡም። እናም ሀድጎን ባገኙት ጊዜ ሁሉ አድጊ ብለው ነበር አሉ የሚጠሩት። አህያ ለማለት። ሀድጎም መረረውና ጃንሆይ ዘንድ ከሰሳቸው።. ንጉሱ አለቃን አስጠርተው ለምን ሀድጊ እያሉ እንደሚሳደቡ ቢጠይቋቸው አይ ጃንሆይ እኔ «አህያ ሸራህያ» እያልኩ ስጸልይ ሰምቶኝ እንጂ አልሰደብኩትም ብለው በብልሀት አመለጡ።