Jump to content

ሄሮዶቶስ

ከውክፔዲያ
የሄሮዶቶስ ሃውልት

ሄሮዶቶስ ወይም ሄሮዶቱስ (ግሪክΗρόδοτος) የጥንታዊ ግሪክ (492-433 ዓክልበ.) ታሪክ ጸሓፊ ነበረ። የታሪክ መረጃዎቹን በሥርዓት በመሰብሰብ እና በማቀናበሩ የታሪክ-አባት በመባል ይታወቃል።

ኢትዮጵያ በሄሮዶቶስ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«ሂስቶሪያይ» (ታሪኮች) በሚባል ጽሑፍ (472 ዓክልበ. ገደማ) ሄሮዶቶስ ስለ «ኢትዮጵያ» ጥንታዊ መረጃ አቅርቧል። በሄሮዶቱስ አስተያየት ኢትዮጵያ ከኤለፋንቲን ደሴት (የአሁኑ አስዋን) ጀምሮ ከግብጽ ወደ ደቡብ የሚገኘው አገር ሁሉ ነው። በወርቅየዝሆን ጥርስዞጲ እንጨት ሀብታም አገር ነው። አንድ ዋና ከተማ በሜሮዌ አላቸው፤ እዚያ አማልክታቸው ዜውስ እና ዲዮናስዮስ ብቻ ናቸው ይላል። በፈርዖን 1 ፕሳምቲክ ዘመን (650 ዓክልበ. ገደማ) ብዙ የግብጽ ወታደሮች አገራቸውን ከደው በኢትዮጵያውያን መካከል እንደ ሰፈሩ ይላል። ከግብጽ 330 ፈርዖኖች፣ 18ቱ ኢትዮጵያውያን (ማለት የኩሽ ፈርዖኖች) ነበሩ ብሎ ጻፈ። ግዝረት ከሚፈጽሙት አገሮች አንድ መሆናቸውን ይመስክራል።

የፋርስ ንጉሥ ካምቢስስ (570 ዓክልበ. ገደማ) ሰላዮችን ወደ ኢትዮጵያውያን እንደ ላከ ሄሮዶቶስ ይነግረናል። ጠንካራና ጤነኛ ሕዝብ አገኙ። ካምቢስስ ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ ቢዘምትም በቂ ስንቅ ባለማዘጋጀታቸው ለሥራዊቱ በፍጹም አልተከናወነምና ቶሎ ተመልሱ።