ህዋስ

ከውክፔዲያ
ለህዋስ መጀመሪያው የሮበርት ሁክ እይታ

ህዋስ (እንግሊዝኛ ሴል) መሰረታዊ የሆነ የህይወት ትንሹ ክፋይ ነው። ሴል በሰወነታችን ውስጥ የሚገኝ ፍጥረት እና ሰውነታችንን ለመገንባት የሚያስፈልግ ነገር ነው። ሴል የሚለው ቃል የመጣው "ሴሉላ" "cellula" ከተሰኘ የላቲን ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ትንሽ ክፍል ማለት ነው።[1]

ሕዋስ የሕይወት መሠረት ነው፡፡እንደ ባክቴሪያ፣ ኘሮቶዞዋ እና እርሾ ያሉት ባለአንድ ሕዋስ ዘአካላት አንድ ሕዋስ ብቻ አላቸው፡፡ይህ የህይወት ያላቸው ነገሮች መስራች ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ሮበርት ሁክ በተባለ እንግሊዛዊ ሳይንቲስት ነበር።

በባለብዙ ሕዋስ ዘአካል(organism) ውስጥ የተለያዩ ሕዋሶች የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ በተግባር የሚመሳሰሉ ሕዋሳት ሕብረ ሕዋስ በመፍጠር ተመሳሳይ ተግባር ያከናውናሉ፡፡ምሳሌ የጡንቻ ህብረ ህዋሳት ተመሳሳይ ተግባር ይፈፅማሉ፡፡ እንዲሁም የሸንዳ ሕብረ ሕዋስ አንድ አይነት ተግባር አላቸው፡፡[2]

የእንስሳት ህዋስ: (1) መንጢብ (2) መነጥብ (3) መካነ ፕሮቲን (4) ቬዞሊ (5) ሻካራ ህዋስ ሰናሶልት (6) ጎልጂ እቃ, (7) ሳይቶስኬሌቶን, (8) ልሙጥ ህዋስ ሰናሶልት, (9) ሃይለ ህዋስ, (10) ፊኝት, (11) ሳይቶሶል, (12) ላይዞዞም (13) ሴንትሪዮል.
  1. ^ "The Origins Of The Word 'Cell'". National Public Radio. September 17, 2010. Archived from the original on 2021-08-05. Retrieved 2021-08-05. "cellŭla". A Latin Dictionary. Charlton T. Lewis and Charles Short. 1879. ISBN 978-1999855789. Archived from the original on 7 August 2021. Retrieved 5 August 2021
  2. ^ የስምንተኛ ክፍል ባዮሎጂ የተማሪ መጽሐፍ