Jump to content

ለቂቅ

ከውክፔዲያ

ለቂቅ ሐሳብ ከውስብስብ ነገሮች ወይንም ሐሳቦች ላይ በአዕምሮ ተነጥሎና ተላቆ የተወሰደ ሐሳብ ማለት ነው።

በተጨባጩ ዓለም፣ የነገሮች ጸባዮች ምንጊዜም ተደባልቀው እንጅ ተለያይተው አይገኙም። ነገር ግን አዕምሮ እነዚህን ጸባዮች ከተደባለቁበት ተፈጥሮ አላቆና ነጣጥሎ መገንዘብ ይችላል። ለምሳሌ አንድን ሎሚ ፣ ሎሚ የሚያስብሉት ፡ የብዙ ጸባዮቹ ተደባለቀው አንድ ላይ መገኘት ነው። ይሁንና አዕምሮ የዚህን ፍሬ ድብልብልነት፣ ቢጫነት፣ የሽታ ዓይነት፣ ክብደት፣ ቁጥር ብዛት ወዘተ... ነጣጥሎ ና ከሎሚው አላቆ መገንዘብ ይችላል። ይሁንና እያንዳንዳቸው ለቂቅ ሐሳቦች፣ በአለም ላይ ለብቻቸው አይገኙም፤ ማለት ቢጫነት፣ ወይንም ድቡልቡልነት ለብቻው በተጨባጩ ዓለም ህልውና የላቸውም።