Jump to content

ለዘለቄታዊ የልማት ግብ

ከውክፔዲያ

‘’’ለዘለቄታዊ የልማት ግብ’’’ ‘’(ኤስ.ዲ.ጂ)’’ ለወደፊቱ ለሚኖር የአለም [አቀፍ ብልፅግና] ግብ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ የተጀመረው በዩናይትድ ኔሽን ሲሆን የተዋወቀው በአለማቀፋዊ ግብ ለዘለቄታዊ ልማት በሚል ነው፡፡ በ2015 መጨረሻ የተጠናቀቀውን [የምእት አመቱን ግብ] የሚተካ ነው፡፡ ኤስ.ዲ.ጂ የሚካሄደው ከ2015 እስከ 2030 ነው፡፡ 17 ግቦች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ 169 ተለይተው የታወቁ አላማዎች አሉት፡፡ [1]

ግቦች ቁጥር በነሀሴ 2015፣ 193 ሀገራት አስራሰባቱን ግቦች ለመከተል ተስማምተዋል፡፡ [2]

  1. ቁጥር ድህነት :ከሁሉም ቦታ ድህነትን ማጥፋት፡፡
  2. ቁጥር ረሀብ :ረሀብን ማቆም፣ የምግብ ዋስትናና በእኩል ጥራት ማግኘትና ዘለቄታዊ ግርናን መደገፍ::
  3. ጥሩ ጤና :ጤናማ ህይወትን ማረጋገጥና ለሁሉም ህድሜ ደህንነትን መደገፍ፡፡
  4. ጥራት ትምህርት :አጠቃላይና ተገቢነት ያለውን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና በህየወት ቀጣይነት ያለው የመማር እድል ለሁሉም መፍጠር፡፡
  5. ፆታ እኩልነት :የፆታ እኩልነትን ማምጣትና፣ ሁሉንም ሴቶችና ልጃገረዶች እድል መስጠት፡፡
  6. ንፁ ውሀና ንፅህና :ለሁሉም ተደራሽና ዘለቄታዊነት ያለው የውሀና የንፅህና አስተዳደርና መኖሩን ማረጋገጥ፡፡
  7. ታዳሽና ተመጣጣኝ ሀይል :ለሁሉም ተመጣጣኝ፣ ተአማኒነት ያለው፣ ዘለቄታዊና ዘመናዊ ሀይል መዳረሱን ማረጋገጥ፡፡
  8. ጥሩ ስራና [[ኢኮኖሚ] :የማያቋርጥ፣ የሚያጠቃልልና ዘለቄታዊነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት፣ የተሟላና ምርታማ ያለው ስራና ተገቢነት ያለው ስራ ለሁሉም፡፡
  9. ፈጠራና ጥሩ የመሰረተ ልማት :ታዳሽ መሰረታዊ ልማቶችን መገንባት፣ የሚያጠቃልልና ዘለቄታዊ የሆነ ኢንዱስትሪአዊና የተስፋፋ ፈጠራን መደገፍ፡፡
  10. አለመመጣጠንን መቀነሰ :በሀገር ውስጥና በሀገራት መሀል ያለውን አለመመጣጠን መቀነስ፡፡
  11. ዘለቄታዊ ከተሞችና ማህበሰቦች :ከተሞችና ሰፈራዎችን የሚያጠቃልሉ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ የሚታድስና ዘለቄታዊነት ያለው ማድረግ፡፡
  12. ፍትሀዊ የሆነ የሀብት አጠቃቀም :ዘለቄታዊ ፍጆታና የምርት አካሄድ መኖሩን ማረጋገጥ፡፡
  13. አየርንብረት ድርጊት :የአየር ንብረት ለውጥና ተፅእኖ ላይ ፍጥነት የለው እርምጃ መውሰድ፡፡
  14. ዘለቄታዊ ውቅያኖስ :ለዘለቄታዊ ልማት ውቅያኖሶችን፣ ባህርንና የውሀ አካላትን በተገቢው ሁኔታ መያዝ፡፡
  15. ዘለቄታዊ የመሬት አጠቃቀም :የመሬት ኢኮሲስተም፣ ዘለቄታዊ የደን አጠባባቅ፣ በረሃማነትን መዋጋት፣ የመሬት መሸርሸርን መከላከልና የባዮዳይቨርሲቲ ላይ የሚከሰቱ ጥፋቶችን መቆጣጠር፡፡
  16. ሰላም እና ፍትህ :ሰላማዊና ሁሉንም የህብረተሰብ አቀፍ ለዘለቄታዊ ልማት ማበረታታት፣ ለሁሉም ተደራሽ የሆነ ፍትሕ ማዳረስና ውጤታማ፣ ተጠያቂና ሁሉን አቀፋዊ አደረጃጀት በሁሉም ደረጃ መገንባት፡፡
  17. ለ [ዘለቄታዊ ልማት] ሽርክና :ለዘለቄታዊ ልማት አለማቀፍ ሽርክናን የሚተገበርበትና የሚዳብርበትን መንቀድ ማጠናከር፡፡
  1. ^ "Technical report by the Bureau of the United Nations Statistical Commission (UNSC) on the process of the development of an indicator framework for the goals and targets of the post-2015 development agenda – working draft" (March 2015). Archived from e%20UNSC%20Bureau%20%28final%29.pdf the original on 4 October 2015. በ1 May 2015 የተወሰደ.
  2. ^ "The Global Goals For Sustainable Development". በ2 September 2015 የተወሰደ.