Jump to content

ሊንጋላ

ከውክፔዲያ
ሊንጋላ የሚናገርበት አውራጃ።

ሊንጋላ (Lingala) ከባንቱ ቋንቋዎች ቤተሠብ አንድ ነው። የሚናገርበት በተለይ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ስሜን-ምዕራብ ክፍል፣ በኮንጎ ሪፑብሊክም፣ እንዲሁም በአንጎላና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ነው። ተናጋሪዎቹ 10 ሚልዮን ናቸው።

የሊንጋላ መነሻ ቦባንጊ በተባለ ቋንቋ ነበር። ከኮንጎ ነጻ መንግሥት አስቀድሞ ቦባንጊ የአከባቢው መደበኛ ቋንቋ ይሆን ነበር። የቤልጅክ ንጉስ አገሩን ከያዙ በኋላ የቀኝ አገሩ መንግሥት ለማስተዳደርና ለመሰበክ ቋንቋውን ጠቃሚ ሆኖ አገኙት። ካለፈው ቦባንጊ እንዲለይ የአዲሱን ቋንቋ ስም ባንጋላ ብለው ጠሩት። ሚስዮናዊዎቹ ወዲያ (1900 አ.ም.) ባንጋላን ዳግመኛ ሲያሻሽሉ "ሊንጋላ" እንዲህ ተፈጠረ።

ሊንጋላ ከፈረንሳይኛ ብዙ ቃሎች ተበድሮ ደግሞ ከፖርቱጊዝ ተጽእኖ አለ (ለምሳሌ "ማንቴካ" = ቅቤ፤ "ሜሳ" = ጠረጴዛ፤ "ሳፓቱ" = ጫማ) ከእንግሊዝኛም ተጽእኖ አለ ("ሚሊኪ" = ወተት፤ "ቡኩ" = መጽሐፍ)።

የጌታ ጸሎት በሊንጋላ

ታታ ዋ ቢሶ፣ ኦዛላ ኦ ሊኮሎ፣
ባቶ ባኩሚሳ ንኮምቦ ያ ዮ፣
ባንዲማ ቦኮንዚ ቧ ዮ፣ ምፖ ኤሊንጎ ዮ፣
ባሳላ ያንጎ ኦ ንሴ፣
ሎኮላ ባኮሳላካ ኦ ሊኮሎ
ፔሳ ቢሶ ለሎ ቢሌይ ብያ ሞኮሎ ና ሞኮሎ፣
ሊምቢሳ ማቤ ማ ቢሶ፣
ሎኮላ ቢሶ ቶኮሊምቢሳካ ባኒንጋ።
ሳሊሳ ቢሶ ቶንዲማ ማሰንጊኛ ቴ፣
ምፔ ቢኪሳ ቢሶ ኦ ማቤ።
Wikipedia
Wikipedia