ሌሊት

ከውክፔዲያ
ሌሊት

ሌሊት ፀሐይ ከጠለቀችበት እስከምትወጣበት ያለው ጊዜ ነው። ይህ ማለት ነጠላ ኮከብ ስለ ሆነ የፈለክዋ ግማሽ በራስዋ ጥላ ስትሆን ነው። ምድር በ፳፬ ሰዓት ውስጥ እየዞረች ነጠላ ፀሐይ እያላት በስተኋላው ጥላ ወይም ሌሊት ይሆናል ማለት ነው።

የፀሐይ ጮራ በጠፈር ተጉዞ ወደ ምድር የሚያንጸባርቀው እቃ እንደ ጨረቃ ሲነካ፣ ይበራል። የብርሃን ፎቶኖች እቃውን ሳይደርሱ ግን ወደ አይኑ አቅጣጫ ስለማይጓዙ አይታዩም፣ ስለዚህ በጨረቃ ዙሪያ ጮራ ቢኖርም ከምድር ጥቁር ብቻ ሊታይ ይቻላል።