ሌይሽመናይሲስ

ከውክፔዲያ
ሌይሽመናይሲስ
Classification and external resources
Skin ulcer due to leishmaniasis, hand of Central American adult 3MG0037 lores.jpg
Cutaneous leishmaniasis in the hand of a Central American adult
ICD-10 B55
ICD-9 085
DiseasesDB 3266 29171
MedlinePlus 001386
eMedicine emerg/296
Patient UK ሌይሽመናይሲስ
MeSH D007896


ሌይሽመናይሲስ ወይም ሌይመኒዮሲስቁንጭር ማለት በሽታ የሚከሰተው በ ፕሮቶዞን  ፓራሳይት  ሌይሽመኒያ በሚባል ዝሪያ እና የሚዛመተውም በተወሰኑ የአሸዋ ዝንብ ዝሪያዎች ንክሻ ነው። [1] በሽታው በሶስት የተለያዩ መንገዶች ሊታይ ይችላል፦ ኩቴኒየስ፣ ሙኮኩቴኒየስ ወይም የውስጥ አካል ሌይሽመናይሲስ ሊሆን ይችላል። [1] ኩቴኒየስ የሚባለው በቆዳ ላይ ሽፍታዎችን/ቁስል በመፍጠር የታይ ሲሆን ሙኮኩቴኒየስ ከቆዳ ባሻገር አፍና አፍንጫንም ያቆስላል። የውስጥ አካል ኩቴኒየስ ደግሞ በቆዳ ላይ ሽፍታ ይጀምርና በመቀጠል ትኩሳት ያስከትላል፣ ቀይ የደም ሴል ቁጥርን ይቀንሳል፣ ጣፊያና ጉበተን ያሳብጣል። [1][2]

በሽታው ሰዎችን የሚይዘው ከ20 ዓይነት በሚበልጡ የ ሌይሽመኒያ ዝሪያዎች አማካየነት ነው። [1] አጋላጭ ምክንያቶች፦ ድህነት፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ የደን መጨፍጨፍ አና የከተሞች መስፋፋት ናቸው። [1] ሦስቱንም የዚህ በሽታ ዓይነቶች ፓራሳይቱን አጉልቶ በሚያሳይ መሳሪያ/በማይክሮስኮፕ በማየት ማወቅ ይቻላል። [1] በተጨማሪም፤ ውስጣዊውን በሽታ በደም ናሙና ምርምራ ማወቅ ይቻላል። [2]

ሌይሽመኒያሲስን በተወሰነ ደረጃ ፀረ ተባይ ኬሚካልየተነከረ የአልጋ አጎበር አድርጎ በመተኛት መከላከል ይቻላል። [1] ሌሎች የመከላከያ እርምጃዎች የአሸዋ ዝንቦችን ለመግደል የሚያስችል የኬሚካል ርጭት ማካሄድና በበሽታው የተያዙ ሰዎች በውቅቱ ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ ስርጭቱን መግታት ነው። [1] የሚያስፈልገው የህክምና ዓይነት የሚወሰነው በሽታው ከምን እንደመጣ፣  በሌይሽመኒያዝሪያና በህመሙ ዓይነት ይወሳናል። [1] ለውስጣዊ በሽታ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት የመድኃኒት ዓይነቶች፦ ሊፖሶማል አምፎትሪሲን ቢ,[3] የ ፔንታቫሌንታንቲሞኒያልስ እና ፓሮሞምሲን ውህድ,[3] እና ሚልቴፎሲንናቸው። [4] ለኩቴኒየስ በሽታ ፓሮሞምሲን፣ ፍሉኮናዞል፣ ወይም ፔንታሚዲን ውጤታማ ሊሆን ይችላል። [5]

በአሁኑ ወቅት 12 ሚሊዮን የመሆኑ ሰዎች በ98 አገሮች [6] በበሽታው ተጠቅተው ይገኛሉ። [2] በየዓመቱ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎእ አዲስ የሚያዙ ሲሆኑ [2] ከ20 እስከ 50 ሺ የሚሆኑት ደግሞ በየዓመቱ በዚህ ምክንያት ይሞታሉ። [1][7] ወደ 200 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በኢሲያ፣ አፍሪካ፣ ደቡብና መካከለኛ አሜሪካ፣ እንዲሁም ደቡብ አውሮፓ ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ይኖራሉ። [2][8] የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ለማከም በአንዳንድ መድኃኒቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ አድርጓል። [2] በሽታው በሌሎች በርካታ እንስሳት ላይ እንደ ውሾች እና አይጠ መጉጦችላይ ይከሰታል። [1]

ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Leishmaniasis Fact sheet N°375". World Health Organization (January 2014). በ17 February 2014 የተወሰደ.
  2. ^ Barrett, MP; Croft, SL  (2012). "Management of trypanosomiasis and leishmaniasis.". British medical bulletin 104: 175–96. doi:10.1093/bmb/lds031. PMID 23137768. 
  3. ^ Sundar, S; Chakravarty, J  (Jan 2013). "Leishmaniasis: an update of current pharmacotherapy.". Expert opinion on pharmacotherapy 14 (1): 53–63. doi:10.1517/14656566.2013.755515. PMID 23256501. 
  4. ^ Dorlo, TP; Balasegaram, M ; Beijnen, JH ; de Vries, PJ  (Nov 2012). "Miltefosine: a review of its pharmacology and therapeutic efficacy in the treatment of leishmaniasis.". The Journal of antimicrobial chemotherapy 67 (11): 2576–97. doi:10.1093/jac/dks275. PMID 22833634. 
  5. ^ Minodier, P; Parola, P  (May 2007). "Cutaneous leishmaniasistreatment.". Travel medicine and infectious disease 5 (3): 150–8. doi:10.1016/j.tmaid.2006.09.004. PMID 17448941. 
  6. ^ "Leishmaniasis Magnitude of the problem". World Health Organization. በ17 February 2014 የተወሰደ.
  7. ^ Lozano, R (Dec 15, 2012). "Global and regional mortality from 235 causes of death for 20 age groups in 1990 and 2010: a systematic analysis for the Global Burden of Disease Study 2010.". Lancet 380 (9859): 2095–128. doi:10.1016/S0140-6736(12)61728-0. PMID 23245604. 
  8. ^ Ejazi, SA; Ali, N  (Jan 2013). "Developments in diagnosis and treatment of visceral leishmaniasis during the last decade and future prospects.". Expert review of anti-infective therapy 11 (1): 79–98. doi:10.1586/eri.12.148. PMID 23428104.