ልዩ ትምህርት

ከውክፔዲያ

የልዩ ፍላጎት ትምህርት ማለት ከመደበኛው ትምህርት በተለየ ሁኔታ የልዩ ትምህርት ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እንደ እውቀታቸው መጠንና እንደ አስፈላጊነቱ በተለየ መልኩ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ የትምህርት አይነት ነው። ልዩ ፍላጎት ትምህርት ራሱን በቻለ በልዩ ትምህርት ቤት ወይም በመደበኛ ትምህርት ቤት ውስጥ በሚገኙ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መስጫ ክፍሎች ውስጥ ወይም በመደበኛ ትምህርት ቤት በመደበኛ ክፍሎች ውስጥ በልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህር የሚሰጥ የትምህርት አይነት ነው።