Jump to content
አማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

ሎጎግራም

ከውክፔዲያ

ሎጎግራፊክ ጽሕፈቶች እያንዳንዱ ምልክት ወይም ሎጎግራም ለአንድ ቃል ይቆማል። የግብጽ ሃይሮግሊፎች መጀመርያ ከሎጎግራም (ስዕሎች) ብቻ ተሠራ። ዕጅግ በጥንት ቅድመ-ታሪክ ዘመን ግን የተናባቢ ምልክቶች እና የክፍለ-ቃል ምልክቶች ተጨመሩለት።

በሌሎቹ ጥንታዊ ሎጎግራም ጽሕፈቶች ደግሞ እያንዳንዱ ምልክት ለቃል ወይም ለክፍለ-ቃል ሆኖ ይጻፍ ነበር። ከነዚህም የትንሹ እስያ ሃይሮግሊፍኩነይፎርም ጽሕፈትየማያ ሃይሮግሊፍ አሉ።

ኣሁን የቻይና ጽሕፈት እንዲሁም ከሎጎግራም ይሠራል። የቻይና ጽሕፈት ከቻይንኛ ጭምር ለሌሎች ልሳናት እንደ ቬትናምንኛኮሪይኛ ቀድሞ ይጠቀም ነበር። ዛሬም የቻይና ምልክቶች በጃፓንኛ ጽሕፈት ደግሞ ይገኛሉ። በቻይና ዙሪያ ሌሎች ተመሳሳይ ጽሕፈቶች ዪ ጽሕፈትታንጉት ጽሕፈትየናቂ ጽሕፈት ይገኛሉ።