Jump to content

አጋጣሚ ዕውነት

ከውክፔዲያ
(ከሐቅ የተዛወረ)

አጋጣሚ ዕውነት ማለት ውሸት ሊሆን ይችል የነበር፣ ነገር ግን ዕውነት የሆነ ረቂቅ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፣ አሁን ካለው ዓለም ሌላ፣ ሌሎች ዓለማት ቢፈጠሩ ኑሮ ፣ በነዚህ አለሞች ዕውነት ሊሆን፣ ወይም ደግሞ ውሸት ሊሆን ይችል የነበር ረቂቅ ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ በፀሐይ ዙሪያ ፱ ፈለኮች አሉ። ይሄ ዕውነት ቢሆንም፣ ነገር ግን ውሸት ሊሆን ይችል የነበር ረቂቅ ነው። ለምሳሌ ከአሁን አለም ሌላ ቢፈጠር፣ በዚያ አለም ፳ ፈለኮች በፀሐይ ዙርያ ቢኖሩ ኖሮ ይችሉ ነበር።

ለምሳሌ፦ የደም ቀለም ቀይ ነው። የደም ቀለም ሰማያዊ ቢሆን ኖሮ ይችል ነበር።

የሳይንስ ዕውቀት መሰረቶች አጋጣሚ ዕውነታዎች ናቸው። በዚህ ምክንያት ሥነ አምክንዮን በመጠቀም ብቻ የአንድ ሳይንሳዊ ዕውቀትን ዕውነታ ማረጋገጥ አይቻልም፣ ምክንያቱም የማንኛውም አጋጣሚ ዕውነት ተቃራኒ ዕውነት ሊሆን ይችል ስለነበር። ስለሆነም የሳይንስ አረፍተነገሮች ከተጨባጩ አለም አንጻር መፈተን ይገባቸዋል። ከአለም ጋር አብረው እሚሄዱ የሳይንስ ዕውቀቶች፣ ቀስ ብለው ኅልዮት በኋላም የተፈጥሮ ኅግጋት ለመባል ይበቃሉ።

ደግሞ ይዩ፦ አስገዳጅ ዕውነት