አስገዳጅ ዕውነት

ከውክፔዲያ

አስገዳጅ እውነት ማለት በምንም ዓይነት መንገድ ውሸት ሊሆን የማይችል ረቂቅ ነው። በሌላ አነጋገር፣ አሁን ካለው ዓለም ሌላ ዓለሞች ቢፈጠሩ ኖሮ እንኳ እውነትነቱ ጸንቶ የሚቆም ወይም ግድ የሚል ረቂቅ ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ 1+1= 2 አስገዳጅ እውነት ነው፣ ምክንያቱም በምንም ዓይነት ውሸት ሊሆን አይችልም። በሌላ አነጋገር አንድ ድመትና እና ሌላ አንድ ድመት፣ ሁለት ድመቶች ከመሆን በስተቀር በምንም አማራጭ ሌላ ሊሆኑ አይችሉም።

ሌላ ምሳሌ ፦ "ነገ ይዘንባል ወይንም አይዘንብም" ቢባል፣ ይሄ ረቂቅ ዓረፍተ ነገር ምንጊዜም እውነት ነው። የፈለገ ነገር ቢፈጠር፣ ወይ ከመዝነብ ወይም ካለመዝነብ ውጭ ሊሆን እሚችል ነገር የለም። ነገ ሊዘንብ እና እንዲሁም በዚያው ጊዜ ላይዘንብ አይችልም!

የሒሳብና የሥነ አመክንዮ ዕውቀቶች እንደዚህ ባሉ አስገዳጅ እውነቶች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፣ ሥለሆነም ማናቸውም የሒሳብ ዕውቀቶች በሥነ አመክንዮ እውነትነታቸው ይረጋገጣል።