ሐይክ

ከውክፔዲያ
የሐይክ ምስል በዬሬቫን.

ሐይክ (አርሜንኛ፦ Հայկ) በአርሜኒያ አፈ ታሪክ ውስጥ የአርሜናዊ ህዝብ መስራች ነበረ። የሱ አፈታሪክ በታሪክ ጸሐፊው ሙሴ ሖሬናዊ 5ኛ ክፍለ ዘመን መጽሐፍ የአርሜኒያ ታሪክ በተለይ የሚገኘው ነው።

ትውልድ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በሙሴ ሖሬናዊ ዘንድ ሐይክ የያፌት ልጅ ጋሜር ልጅ የቶርጎም (ቴርጋማ) ልጅ ነው[1]። ሐይክ ደግሞ የሐይካዙኒ ሥርወ መንግሥት መስራች ይባላል። በታሪክ ጸሐፊው ጇንሸር ዘንድ፣ ሐይክ 'የሰባት ወንድማማች መስፍን ሆኖ፣ መጀመርያ ዓለሙን በሙሉ እንደ ንጉሥ ለነገሠው ለረጅሙ ሰው ለናምሩድ ያገልግል ነበር'።

'ሐይክ' ደግሞ በአርሜንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የኦሪዮን ከዋክብት ስም ነው። (ኢዮብ 38፡31)

በሙሴ ሖሬናዊ መጽሐፍ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በሙሴ ሖሬናዎ መሠረት፣ በባቢሎን እየኖረ የቶርጎማ ልጅ ሐይክ ልጁን አርማኔያክን ከወለደ በኋላ፣ ትዕቢተኛው ቲታናዊቤል (እሱም ሙሴ እንደሚለው ናምሩድ ነው) እራሱን የአለም ሁሉ ንጉሥ ስላደረገ፣ ሐይክ ከቤተሠቦቹ ከ300ም ሰዎች ጋራ ወደ አራራት አገር ፈልሶ ሐይካሸን የተባለ መንደር ይመሠረታል። በመንገዱ ላይ ለልጅ-ልጁ ለካድሞስ አንድ ሠፈር ይተወዋል። ሐይክ ወደ ባቢሎን እንዲመልስ ግድ እንዳለው የሚል መልእክት ለማቅረብ ቤል ከልጆቹ አንዱን ወደ ሐይክ ልኮ እሱ ግን እምቢ ይለዋል። ከዚያ ቤል ከግዙፍ ሠራዊቱ ጋራ በሱ ላይ ቢዘምትም ካድሞስ ግን ስለመቅረቡን ሐይክን ያሳውቀዋል። ሐይክ የራሱን ሠራዊት በቫን ሐይቅ ዳርቻ ሰብስቦ የቤል ባርዮች እንዳንሆን ወይም ቤልን አሸንፈን መግደል ወይም በሙከራው መሞት አለብን ብሎ ይላቸዋል።

የቤል ድልና ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከዚያ በኋላ ሐይክ የቤልን ሠራዊት በአንድ ተራራ ላይ ያገኛቸዋል። ሙሴም ይህን ተራራ በዳስታከርት ሥፍራ እንደሚገኝ ይላል። ቤል እራሱ በሠራዊቱ ፊት ይታያል። በፍልሚያው መኅል ሄይክ በእድለኛ ፍላጻ ቤልን ገድሎ ሠራዊቱ ተደናገረና ድል ሆነ።

በሌሎች ደራሲዎችም ዘንድ፣ ይህ ፍልሚያ በቫን ሐይቅ ደቡብ-ምሥራቅ በጁላመርክ ዙሪያ በበድዩጻዝናማርት ከክርስቶስ በፊት በ2501 አመታት ነበረ[2]

'ሐይካበርድ' የተሰየመ አምባ በውጊያው ሥፍራ ላይ መሠርቶ ስሙ 'ሐይካሸን' የተባለ መንደር ይሠራል። የፍልሚያው አገር 'ሐይክ' ይለዋል፤ የዛሬም አርሜኒያ ስም 'ሃያስታን' የአርሜኒያም ሕዝብ 'ሃይ' ይባላል። እንዲሁም በጥንት በኬጢያውያን ጽሕፈቶች በዙሪያው ሐየሣ የተባለ ብሔር ነበረ።

ዋቢ ጽሑፎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ የሙሴ ሖሬናዊ አርሜኒያ ታሪክ 1.5 [1] (በሩስኛ)
  2. ^ Razmik Panossian, The Armenians: From Kings And Priests to Merchants And Commissars, Columbia University Press (2006), ISBN 978-0231139267, p. 106.
  • P. Kretschmer. "Der nationale Name der Armenier Haik"
  • Vahan Kurkjian, "History of Armenia," Michigan, 1968[2]