መላኩ ወረደ

ከውክፔዲያ

መላኩ ወረደ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከኣሉ ስምንት የተለያዩ የእጽዋት ክምችቶች ከኣሉበት ኣገሮች ኣንዷ ናት። ኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ በደረሰው ድርቅና ጠኔ የተነሳ የኣገርዋ የሰብል ዘሬች እንዳይጠፉ በመሰብሰብና እንዳስፈላጊነቱም መልሶ ለገበሬዎች በመስጠት ዶ/ር መላኩ ወረደ የሚደነቅ ሥራ ኣከናውነዋል። የሥራቸውም ውጤት ከኣፍሪቃ ተርፎ በዓለም ከኣሉት ኣስተማማኝ ክምችቶች ኣንዱ ሆኗል። ዶ/ር መላኩ በእርሻ ማልማት ላይ የብዙኅ ሕይወትን ለመጠበቅና ለማብዛት እንደሚቻል ያሳወቁ፣ ያረጋገጡ ፈር ቀዳጅ ተመራማሪ ስለመሆናቸውም ዓለም አቀፍ ዘገባዎች ይመሰክራሉ።

ዶ/ር መላኩ ወረደ ይህ የእጽዋት ክምችት እንዳይጠፋ በኣለፉት ኣያሌ ዓመታት ትልቅ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። ለእዚህም ሥራቸው “ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ” ወይም “Right Livelihood Award” የሚባል ሽልማት በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ተሰጥቷቸዋል።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]