መሰላል

ከውክፔዲያ
መሠላል

መሠላል ቀጥ ያለ ወይንም ያጋደለ መወጣጫ ነው። ሁለት አይነት ሲሆን እነርሱም ቋሚ መሠላል እና የገመድ መሰላል ናቸው። ቋሚ መሰላል የሚባለው ከእንጨት ወይም ከብረት አልያም ደግሞ ከሌሎች ነገሮች ሊሰራ የሚችል የመሰላል አይነት ነው። ይህም ሁለት ረዣዥም ቋሚ እና በእነዚህ ቋሚዎች ላይ የሚመቱ ወይንም የሚታሰሩ በርከት ያሉ አጫጭር መወጣጫዎች እንዲኖሩት ተደርጎ ይሰራል። ይህ አይነቱ መሰላል ሊወጣበት ወደተፈለገው ቦታ እንዲያጋድል ተደርጎ ይቀመጥ እና ጥቅም ላይ ይውላል። ሁለተኛው የመሰላል አይነት የገመድ መሰላል ሲሆን ይህ ደግሞ የሚሰራው ከገመድ ነው። ጥቅም ላይ ሲውል ግን ከላይ ብቻ ይንጠለጠላል።