መሰረት መፋለስ
የአምክንዮ -ምክነት ብዙ ጊዜ ሚመጣው አንድን ወይም ብዙን እውነት ከሌላ ከፍተኛ እውነት ጋር ለማያያዝ በሚሞከርበት ጊዜ በሚደረግ ስህተት ነው።
ከዚህ በተረፈ ግን፣ የሒሳብና የፍልስፍና ተማሪወች በተለምዶ የአምክንዮ-ምክነት የሚሉት የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ አለ። እሱም የመሰረት-መፋለስ ይባላል። ይህ ምክነት፣ ጸጉር እንሰንጥቅ ከተባለ፣ የአምክንዮ ምክነት አይደለም። እውነትን ከእውነት በማስተሳሰር ላይ የትነሳ ምክነት ሳይሆን፣ ገና ከመነሻው በውሽት ላይ የተመሰረተ ውድቀት ነው። በዚህ ዋና ዘርፍ ስር የሚንቀሳቀሱ 3 ዋና ዋና ምክነቶች ይገኛሉ፦
1ከዝንጀሮ ቆንጆ /false dilemma/bifurcation
በአንድ ሁኔታ /አጋጣሚ , ከሁለት በላይ ምርጫ እያለ , ሁለት ብቻ ምርጫ ማቅረብ ::
ምሳሌ :- Quote: «ወይ ከኛ ጋር ናችሁ ወይ ደግሞ ከአሸባሪወች።»
ይህ አባባል እንግዲህ አንድ ሰው ከሁለቱም ውጭ መሆን እንደሚችል ከስረ -መሰርቱ በሀሰት ክዷል።
ምሳሌ፦ Quote: አበበ (በስልክ )- ረጅም ነሽ ? አለሚቱ (በስልክ )- አይደለሁም ! አበበ - እንግዳው አጭር ነሽ ማለት ነው።
አበበ ያለተረዳው፣ አለሚቱ መካከለኛ ቁመት ሊኖራት እንደሚችል ነው።
2. የሚጠልፍ ጥያቄ /complicated question
ምሳሌ Quote: ፖሊስ ለአለሙ : «የሰው ቤት መዝረፍክን አቆመሀል ?»
እንግዲህ አለሙ፣ አወ ካለ ካሁን በፊት ሲዘርፍ ነበር ማለት ነው። አይ ካለ ደግሞ በስራው እየቀጠለበት ነው ማለት ነው። ይህ እንግዲህ የ ከዝንጀሮ -ቆንጆ አይነት ምክነት ነው። ጥያቄው በራሱ፣ ከስር መሰረቱ ምርጫን በሰው -ሰራሽ መንገድ በ 2 በመወሰን ምክነት ሰርቷል።
3.ክብ አምክንዮ / circular logic
መነሻ የመድረሻ ደጋፊ ነው የመነሻ Laughing ክብ እየሰሩ አንድን ነገር ለማሳመን መሞከር ማለት ነው።
ምሳሌ፦ Quote: ደበበ ፦ አቶ አለሙ የሚያምኑበትን ብቻ ነው ሚናገሩት። ደበበ ፦ ስለዚህ አቶ አለሙ አይዋሹም።
አንድ ሰው የሚያምነው ነገር ውሸት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፦ ወባ ሲይዘው ቡዳ በላኝ ብሎ ሊያምን ይችላል። ያ ሰው የሚያምንበትን ቢናገር የግዴታ እውነት ተናገረ ማለት አይደለም። አቶ አለሙ አይዋሹም የሚለው አባባልና አቶ አለሙ ያመኑበትን ይናገራሉ የሚለው፣ ህሉለት በክባ ሁኔታ ተቆራኝተዋል፣ አንዱ አንዱን ይደግፋል ለዛም ነው የነገሩን ስህተት በቀላሉ ማወቅ ሚያዳግተው።
3. እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ እንዲህ አያደርግም / no true scotsman
ምሳሌ ፦ Quote: አለሚቱ ፦ አቶ ማሞ እኮ ሚስታቸውን ፈተው የሚስታቸውን እህት አገቡ :: በቀለ ፦ እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ እንዲህ አያደርግም አለሚቱ ፦ አቶ ማሞ እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ አይደሉም በቀለ ፦- ልክ ነሽ