መናፍቅ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

መናፍቅ መንፈቅ ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን፣ መንፈቅ ማለትም ግማሽ ማለት ነው። መናፍቅ ማለት ከፍሎ የሚያምን ሙሉ እምነት የሌለው ማለት ነው። በክርስትና ትምህርት የማያምን ሰው መናፍቅ አይባልም። ከሀዲ ወይም አህዛብ ይባላል እንጂ።

ክርስትና ትምህርት አምናለሁ ብሎ ነገር ግን ሙሉ የክርስቶስንና የአባቶች ውሳኔዎችን የማይቀበል አካል መናፍቅ ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለአምላክ ማንነት የሚናገረውን የማይቀበል፡ የአምላክን ፈቃዳትና ትእዛዛት በተዛባ መልኩ የሚያስተምር መናፍቅ ይባላል።

ለምሳሌ፡

1. መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ በአንድነት በሦስትነት ይኖራል እያለ አምላክ አንድ አካል ብቻ አለው የሚሉ መናፍቃን ይባላሉ፡፡

2. መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው እያለ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የማይቀበሉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ልጅ ሳይሆን የአብ ፍጡር ነው የሚሉት መናፍቃን ይባላሉ።

3. የእግዚአብሔር ቃል ሰው ለመዳን እምነትና ሥራ ያስፈልገዋል እያለ ድህነት በእምነት ብቻ ነው የሚሉ እንደ ቃሉ መናፍቃን ይባላሉ።

4. በቅዱስ ቃሉ (በመጽሃፍ ቅዱስ)ያልተጻፈውን አይነት የሚያመልኩ፣ በቃሉ ላይ የሚጨምሩና የሚቀንሱ፥ እንዲሁም የቃሉን ትርጉም የሚያንሻፍፉ መናፍቅ ይባላሉ፠