መንግሥተ አክሱም

ከውክፔዲያ

መንግሥተ አክሱም ከደቡብ አረቢያ፣ ቀይ ባህርን ተሻግሮ እስከ ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የአሁኗ ኢትዮጵያ፣ ምስራቃዊ ሱዳን እና ኤርትራን ያማከለ ግዛት ነው። ግዛቱም በብዙ ምሁራን መሰረት ከ1ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎቹ ከዳዕመት 100 አመት በፊት የነበሩ ህዝቦች ናቸው ይላሉ። አክሱም ከተማ ዋና የግዛቱ መዲና ስትሆን በመካከለኛው ዘመን ጀምሮ ይደርስባቸው የነበረው ተከታታይ ወራራዎች ሳቢያ ጃርማ የተባለች ትንሽዬ ከተማ ተሸጋገሩ። በ3ተኛው ክፍለ ዘመን ፋርሳዊው ነብይ ማኒ የአክሱም ግዛት ከነሮማ፣ ከፋርስና፣ ከቻይና ግዛቶች የሚወዳደረው ሀያል ነበረ ብሎ ፅፏል። አክሱማውያን በዘመኑ ከግሪክና ከሮማ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው። በዚህም የተነሳ ግሪካውያን ለአክሱም መንግስታት ትልቅ የባህል ትስስር ነበራቸው። በመጨረሻም የግሪክ ቋንቋ በአክሱም ግዛት ውስጥ እንደ ዋነኛ ቋንቋ ሆኖ አገልግሏል። ይህም ግዕዝ በአራተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የግሪክን ቋንቋ ተክቶ እንደዋነኛ ቋንቋ መሆን ጀምሯል። የአክሱም ስርወ መንግስት ለኢትዮጽያ ሀያልነት መነሳት ትልቅ ምንጭ ነው። በንጉስ ኢዛና ዘመን ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ በአባ ሰላማ አማካኝነት የአክሱም ዋና ሀይማኖት ሊሆን ችሏል። የአክሱም ድንበር ከ4ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ መለጠጥ ጀመረ ነገር ግን በደቡብ አረቢያ ባለው ግዛቶቿ በተደጋጋሚ በፋርስና በአረብ ውቅር ሃይሎች አታለች። ይህም የእስልምና ሀያልነት ከተነሳ ጀምሮ ግዛቱም መዳከም ሲጀምር በ9ኛው ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት የተባለች ከደቡብ ክልል የመጣች የአህዛብ ንግስት የአክሱማውያን ሀይል እንዲዳከምና እንዲፈርስ አድርጋለች። ዮዲት ቤተ ክርስቲያናትን በማቃጠልና ክርስቲያንን በመጨፍጨፍ በመጥፎ ስም የምትታወቅ ናት።