መግነጢስ መስክ


የመግነጢስ መስክ ማለቱ አንድ መግነጢስ ጉልበት የሚያሳርፍበት ከባቢ ዙሪያ ነው። መስኩ ከጉልበት መስክ የተሰራ ሲሆን አፈጣጠሩም በሚንቀሳቀሱ የኤሌክትሪክ ሙላቶች፣ ከጊዜ አንጻር በሚለዋወጥ የኤሌክትሪክ መስክ እና በራሳቸው በአተም እኑሶች የተፈጥሮ መግነጢሳዊ ባህርይ ናቸው። የመግነጢስ መስክ በአንድ ነጥብ ላይ ባለው ጥንካሬ እና አቅጣጫ ይወሰናል፣ ስለሆነም የቬክተር መስክ አይነት ነው ። መግነጢሳዊ መስክ ብዙ ጊዜ የሚተረጎመ በተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ ሙላቶች ላይ በሚያሳርፈው ሎሬንዛዊ ጉልበት ነው።
መግነጢሳዊ መስክ ከጥንት ጀምሮ ለሰው ልጆች ጠቀሜታን አበርክቷል። ለምሳሌ ምድር በምታፈልቀው መግንጢሳዊ መስክ ምክንያት ሰወች ኮምፓስ ሰርተው አለምን እንዲዞሩ አስችሏል። በአሁኑ ዘመን ተሽከርካሪ የመግነጢስ መስኮች ኤሌክትሪክ ለማመንጨትና የኤሌክትሪክ ሞተሮችን ለማንቀሳቀስ በመርዳት የዘመናዊ ህይወት መሰረቶች ናቸው።
ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]