መጽሐፍ

ከውክፔዲያ
መጻሕፍት

መጽሐፍ ማለት ብዙ የጽሑፍ ገጾች ለማንበብ ምቾት የተቀነባበሩበት ወረቀት ክምችት ነው። በተለምዶ የመጽሐፉ አርዕስት በሽፋኑ ፊት ላይ ይታተማል።

አሁን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጽሐፍም በኢንተርኔት ላይ ማንበብ ይቻላል። ሆኖም የተለመደው የወረቀት መጽሐፍ ትልቅ ጥቅም ስላለው ለዘለቄታ የተወደደ ሆኗል።