ሙሉቀን መለሰ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search


ሙሉቀን መለስ (፲፱፻፬፭ ዓ.ም. ተወለደ[1]) የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን ዘፋኖች መሃል አንዱ ነው። 1960 ና 1970ዎቹ በርካታ ዘመናዊ ዘፋኞች የታዩበት ወቅት ነበር። ሙሉቀን መለስን ለየት የሚያደርው ቢኖር ባሀላዊውን ከዘመናዊው በማዋሃድ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለማሳደግ ያደረገው ጥረት ነው።

ሙሉቀን መለስ ባሁኑ ጊዜ በአሜሪካን አገር በዋሽንግተን ዲሲ ሙሉ ጊዜ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት አገልጋይ ሲሆን ያለውን ድንቅ ችሎታ ላመነበትና ለሚያምንበት ሃይማኖት አውሎ አሁንም እጹብ ድንቅ ድምጽ ካላቸው የመንፈሳዊ ዘማሪዎችም አንዱ ነው።

የህይወት ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሙሉቀን መለሰ በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ገና የ፲፫ ዓመት ልጅ እያለ ድምጻዊነት ሙያውን በፈጣን ኦርኬስትራ በመጀመር በ፲፱፻፷ ዓ.ም. ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ ክፍል ገብቶ ዝነኛነቱን አሳውቋል። ሙሉቀን በሙዚቃ ዓለም በነበረበት ጊዜ በርካታ ዜማዎች የተጫወተ ሲሆን ዜማዎቹም በሸክላ ተቀርጸው ወጥተዋል።[1]

«እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ፤ የፊት ጉዴን ትታ እደግ ማሞ አለችኝ» የተባለችው ዜማ የመወደድዋን ያህል ድምጻዊው ሙሉቀን መለሰም ተደናቂ ሆኗል። ሙሉቀን መለሰ እንደዚሁም፦ «ወንበር ተደግፎ ክብ ጠረጴዛ የሰነፎች በትር ትችት በጣም በዛ» እያለ የሚጫወታት ዘፈንም ሙሉቀንን ታዋቂና ዘፈኖቹንም ተወዳጅ አድርጎታል።[1]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 27-28