ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና በሰው ልጅን ማኅበራዊ ባህርይ ላይ የሚመራመር የፍልስፍና ዘርፍ ነው። የማሕበራዊ ማንነት፣ የፖለቲካዊ ሥነ ምግባር፣ የተለያዩ ር ዕዮተ ዓለሞችን፣ የሚዎጡ ኅግጋት ፍትሃዊነትን፣ የሥነ ልቡናን ፍልስፍናዊ መሰረቶች፣ እና መሰል የቡድን ጠባያትን የሚያጠና ክፍል ነው።

በዚህ የ ዕውቀት ሥር ከሚካለሉ ውስጥ፣ ማኅበራዊ ሥነ ኑባሬ እና ማኅበራዊ ሥነ ዕውቀት እንደ ቅርንጫፍ ሊዎሰዱ ይችላሉ።

በማኅበራዊ ሥነ ኑባሬ «ማኅረሰቦች ኑባሬ አላቸውን? አንድ ማኅበረሰብ አለ ከተባለ፣ በውስጡ ካሉት አባላት ግለሰቦች ይለያል? ከተለየስ በምን ዓይነት ሁኔታ?» የሚሉት ጥያቄዎች ይመረመራሉ።

በማኅበራዊ ሥነ ዕውቀት «የአንድ ግለሰብ ዕውቀት በማኅበረሰቡ የቱን ያክል ጫና ይደረግበታል? ማኅበራዊ ተቋማት በአንድ ግለሰብና በአጠቃላይ ማኅብረሰቡ ዕውቀትና እምነት ላይ ምን አስተዋጽዖ ያደርልጋሉ?» የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክራል።

ስለሆነም ይህ የፍልስፍና ዘርፍ ከፖለቲካ እና ሥነ ባሕል ጥናቶች ጋር ተነባባሪ ክፍሎች አሉት።