ማንግ

ከውክፔዲያ

ማንግ (ቻይንኛ፦ 芒) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር። ሌላ ስሙ ኋንግ (荒) ነው።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገቡት ድርጊቶች እንዲህ ናቸው፦ በ1826 ዓክልበ. ግድም አባቱ ኋይ ዓርፎ ማንግ ተከተለው። በዚያውም ዓመት ጨለማውን (የዳ ዩን) ዱላ ይዞ የሆ አገረ ገዥ ለመቀበል ሄደ። በ፲፫ኛው ዓመት (1813 ዓክልበ. ግ.) ወደ ምሥራቅ እስከ ባሕር ድረስ በሄደበት ጊዜ አንድ ታላቅ ዓሳ አጠመደ። በ፴፫ኛው ዓመት (1783 ዓክልበ. ግ.) የሻንግ ልዑል ወደ ዪን ተዛወረ።

በ፶፰ኛው ዓመት (1769 ዓክልበ. ግ.) ዓረፈና ልጁ ተከተለው። በሌላ ምንጭ ዘንድ ግን ማንግ ቻይናን የገዛው ለ፲፰ ዓመታት ብቻ ነበረ።

ቀዳሚው
ኋይ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1826-1769 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ